Homeዜናና ወቅታዊዜናወረዳዎች በነጋዴዎች ላይ የሚወስዱትን ርምጃ የሚገድብ መመርያ በሥራ ላይ ሊውል ነው

ወረዳዎች በነጋዴዎች ላይ የሚወስዱትን ርምጃ የሚገድብ መመርያ በሥራ ላይ ሊውል ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ወረዳዎች በከተማዋ ነጋዴዎች ላይ ከሚወስዱት ርምጃ ጋር በተገናኘ ያዘጋጀውን “የመንደር የንግድ ቁጥጥር የአሠራር ሥርዓት” የተሰኘ መመሪያ አወጣ፡፡ በአዲሱ መመርያ መሠረት የንግድ ቤቶች በወረዳዎች ሊታሸጉ የሚችሉት የንግድ ሥራ ፍቃድ ሳያሳድሱ ሲቀሩ ወይም በተሠረዘ የንግድ ሥራ ፍቃድ ሲሠሩ ብቻ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ በቀጣይ የሚተገብረው አሠራር ባለፈው ሳምንት በፍትሕ ሚኒስቴር የምዝገባ ሂደቱ ማጠናናቀቁ ተገልጧል፡፡

ቢቢሲ አማርኛ የከተማዋ ንግድ ቢሮ የንግድ ክትትል እና ቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ቅድስት ሥጦታው ነግረውኛል ሎ እንደዘገበው፣ መመርያው የወጣው በነጋዴዎች ላይ የሚወሰዱ ርምጃዎችን ፍትሐዊነት በተመለከተ አልፎ አልፎ የሚነሱ ችግሮች በመኖራቸው ነው፡፡

ምክትል ቢሮ ኃላፊዋ ከርምጃ አወሳሰድ ጋር ተያይዞ ‘አላግባብ ታሸገብን፣ አላግባብ ተከፈተ’ የሚሉ ቅሬታዎች እንደሚነሱ መናገራቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡

በአዲስ አበባ ወረዳዎች፤ ከዚህ ቀደም በነጋዴዎች ላይ እስከ ማሸግ የሚደርስ ርምጃ ሲያወስዱ ጥሰቶች ነበሩ፡፡ እነዚህ ጥሰቶች የእቃዎች ዋጋ ዝርዝር አለመለጠፍ፣ ደረሰኝ አለመቁረጥ፣ ጤናማ ያልሆኑ ምርቶችን ማቅረብ፣ አድራሻ ለውጥ አለማሳወቅ እና ትክክለኛ የመለኪያ መስፈሪያ አለመጠቀም ይገኙበታል፡፡

ሆኖም አዲሱ መመርያ ይህን እርምጃ መውሰድ በተመለከተ ኃላፊነቱን ከወረዳዎች ላይ አንስቷል፡፡ መመርያው የወረዳው የክትትል እና ቁጥጥር ባለሞያዎች በነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር የሚያደርጉባቸውን 25 ጉዳዮችን ዘርዝሯል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ ከንግድ ፍቃድ፣ ከደረሰኝ፣ ከጤና፣ ከመለኪያዎች እንዲሁም ከንግድ ቦታ አድራሻ ጋር የተያያዙ ጥሰቶች ይገኙበታል። ባለሞያዎች ለእነዚህ ጥሰቶች ከዚህ ቀደም እንደሚያደርጉት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት እና ማሸግ የማይችሉ ሲሆን ርምጃ መውሰድ የሚችሉት ከንግድ ፍቃድ ጋር በተያያዙ ሁለት ጥሰቶች ላይ እንደሚሆንም መመርያው ደንግጓል።

በአዲሱ መመርያ ላይ የወረዳ ባለሞያዎች በነጋዴዎች ላይ ርምጃ የሚወስዱት የንግድ ሥራ ፍቃድ ሳይኖራቸው ንግድ ላይ ተሠማርተው ሲያገኗቸው እንዲሁም የንግድ ሥራ ፍቃድ ሳያሳድሱ ወይም በታገደ ወይንም በተሰረዘ የንግድ ሥራ ፍቃድ ከሠሩ ነው፡፡

የወረዳ ባለሞያዎች በእነዚህ ጥፋቶች ላይ እርምጃ ከመውሰዳቸው አስቀድሞ ለቅርብ ኃላፊ በጽሑፍ ማሳወቅ እንዳለባቸው የሚደነግገው መመርያ፣ ርምጃ የማስወሰዱን ውሳኔ ለከተማዋ የንግድ ቢሮ ሰጥቷል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በንግድ ቢሮ ፍቃድ አውጥተው የሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎች ብዛት ከ400 ሺሕ በላይ ነው፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular