Homeዜናና ወቅታዊዜናሳዑዲ ዐረቢያ ምዕመናን በዑምራ ቪዛ ወደ መካ ከተማ መግባት የሚችሉት ለቀጣይ ሦስት...

ሳዑዲ ዐረቢያ ምዕመናን በዑምራ ቪዛ ወደ መካ ከተማ መግባት የሚችሉት ለቀጣይ ሦስት ቀናት ብቻ ነው አለች

የሳዑዲ ዐረቢያ ሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር የዑምራ ቪዛ የያዙ ምዕመናን ወደ መካ መግባት የሚችሉትን ቀነ ገደብ አስቀመጠች፡፡ ሚኒስቴሩ ከጁመዐ ግንቦት 16 አንስቶ እስከ ሰኔ 19//2016 የሐጅ ቪዛ የያዙ ምዕመናን ብቻ ወደ መካ መግባት እንደሚችሉ ገልጿል፡፡

የዑምራ ቪዛ የያዙ ምዕመናን ላይ ቀነ ገደብ ያስቀመጠችው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ ከግንቦት 1/2016 ጀምሮ ከመላው ዓለም ለሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ሑጃጆችን በመቀበል ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡ ከሑጃጀቹ መካከል 45 ኢትዮጵያውንን የያዘው የሳዑዲ አየር መንገድ አውሮፕላን ንጋት ላይ መዲና መድረሱ ተነግሯል፡፡

ከመላው ዓለም ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሑጃጆችን የምታስተናግደው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ ሑጃጆችን ብቻ ለማስተናገድ በሚል ካስቀመጠችው ቀነ ገደብ በኋላ ያለ ሐጅ ቪዛ ወደ መካ የሚገቡ ምዕመናን ላይ መቀጮ እንደምትጥል ከዚህ ቀደም ማሳሰቢያ መስጠቷ ይታወሳል፡፡ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር ያወጣው የመቀጮ ደንብ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው በሚቀጥለው ሳምንት ግንቦት 25/2016 ነው፡፡

ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ያለ ሐጅ ቪዛ ወደ መካ ከተማ የሚገቡ ምዕመናን ላይ የሚጣለው የገንዘብ መቀጮ 10 ሺሕ የሳዑዲ ዐረቢያ ሪያል ነው፡፡ መቀጮው ተፈጻሚ የሚሆነው ከውጪ ሀገራት ወደ ሳዑዲ የሚገቡ ምዕመናን ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በሀገሪቱ ዜጎችም ላይ ነው ተብሏል፡፡ ደንቡን በተደጋጋሚ የሚጥሱ የውጪ ሀገራት ዜጎች 100 ሺሕ ሪያል ተቀጥተው ከሳዑዲ እንደሚባበሩ እንዲሁም ዳግመኛ እንዳይገቡ እገዳ እንደሚጣልባቸው የሐጅ እና ዑምራ ሚኒቴር መግለጫ ያመለክታል፡፡

አዲሱ ደንብ ከምዕመናን በተጨማሪ የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡ በዚህም ያለ ፍቃድ የትራንስፖርት አገልግሎ በሚሰጡ ላይ የ6 ወር እስር እንዲሁም 50 ሺሕ ሪያል መቀጮ ይጣላል፡፡ የትራንስፖርት አገለግሎት ሰጪው የሚጠቀምበት ተሽከርካሪ ሊወረስ እንደሚችልም ደንቡ ያትታል፡፡ [ሚንበር ቲቪ]

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular