እሑድ , ذو الحجة 17, 1445
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናየኢራኑን ፕሬዝዳንት ኅልፈት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ

የኢራኑን ፕሬዝዳንት ኅልፈት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ

የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ተሳፍረውባት በነበረው ሄሊኮፕተር በደረሰው አደጋ ሕይወታቸው የማለፉ ዜና ይፋ ከተደረገ በኋላ በዛሬው እለት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ፡፡ ነዳጅ በዛሬ ውሎ የ0.31 በመቶ ጭማሬ ተመዝግቦበታል፡፡

ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴይን አሚር ዐብዶላሂያንና ሌሎች ባለሥልጣናትን አሳፍራ የነበረችው ሄሊኮፕተር ትናንት እሑድ የተነሳችው ከጎረቤት አዘርባጃን ነበር፡፡ ራይሲ በአዘርባጃን በነበራቸው ቆይታ ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ጋር ሀገራቱ በጋራ ያስገነቡትን ድልድይ አስመርቀዋል፡፡

በዚህ ምርቃት ሥነ ሥርዐት ላይ ለመታደም ሬይሲን ከጫነችው ሄሊኮፕተር ውጪ ሌሎች ሁለት ሄሊኮፕተሮች እርሳቸውን ያጀበ ልዑክ በመጫን ወደ አዘርባጃን በረራ አድርገዋል፡፡ ሆኖም ራይሲን የጫነችው ሄሊኮፕተር በኃይል ለማረፍ ተገዳለች፡፡

ከዚህ ክስተት በኋላ ፕሬዝዳንቱን የጫነችውን ሄሊኮፕተር ፍለጋ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች፣ ሥምሪት ማድረጋቸው ተነግሮ ዛሬ ማለዳ ላይ ራይሲና ሌሎች ባለሥልጣናት ሕይወት እንዳልተፉ የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

የዜናውን ይፋ መደረግ ተከትሎ በዛሬው እለት የብሬንት ነዳጅ ዋጋ በመጨረሻው ገበያ ከነበረበት የአንድ በርሜል ዋጋ ከ83.88 የአሜሪካ ዶላር፣ በ0.31 በመቶ ጨምሮ በ84.24 ተሽጧል፡፡ ነዳጅ ላኪ ሀገራትን ያቀፈው ኦፔክ በቅርቡ እንዳስታወቀው፣ የኢራን እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት 3 ሚሊዮን በርሜል ነው፡፡ በዚሁ ምክንያት የራይሲ ድንገተኛ ኅልፈት ገበያው ላይ ተፅዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችል ተንታኞች ይናገራሉ፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments