Homeዜናና ወቅታዊዜናደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት ፈጽማለች...

ደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት ፈጽማለች በሚል ያቀረበችውን ክስ ግብጽ በይፋ ተቀላቀለች

ግብጽ፤ ደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት ፈጽማለች በሚል ያቀረበችውን ክስ መቀላቀሏ በይፋ ገለጸች፡፡ ሀገሪቱ ክሱን የተቀላቀለችው እስራኤል በፍልስጤማዊያን ንጹሐን ላይ የምታደርሰውን ጥቃት በመቀጠሏ ምክንያት መሆኑን አስታውቃለች፡፡

ደቡብ አፍሪካ ከዚህ ቀደም በዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት ባቀረበችው ክስ “እስራኤል የፈፀመቻቸው ድርጊቶች በባሕሪያቸው የዘር ማጥፋት ወንጀል የመፈጸም እንዲሁም የፍልስጤምን ዘር ለማጥፋት ያለመ ነው” ብላ ነበር፡፡ ይህን የደቡብ አፍሪካ ክስ ኮሎምቢያ እና ቱርክ በይፋ መቀላቀላቸው ይታወቃል፡፡

የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት እሑድ እንዳስታወቀው፣ የቀጠለው እስራኤል በጋዛ በንጹሐን ላይ የምትፈጽመው ጥቃት ፍልስጤማዊያንን ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ከቷል፡፡

ደቡብ አፍሪካ በጥር ወር ያቀረበችውና አሁን በግብጽ ድጋፍ የተቸረውን ክስ የሚመለከተው ዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት መቀመጫውን ያደረገው በኔዘርላንድ ሄግ ከተማ ነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፍርድ ቤት የሆነው የፍትሕ ፍርድ ቤቱ፣ በሀገራት መካከል አለመግባባቶችን ከመፍታት ባለፈ በዓለም አቀፍ የሕግ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ይሰጣል።

የሚሰጣቸው አስተያየቶች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የሕግ አካላት ከፍተኛ ተሰሚነት አላቸው።

እስራኤል ከመስከረም 2016 አንስቶ በጋዛ እየፈጸመች በምትገኘው ጥቃት ቢያንስ 34 ሺሕ ንጹሐን ፍልስጤማዊያን ተገድለዋል፡፡ ከተገደሉት መካከል በርካታ ሕፃናት እና እናቶች ይገኙበታል፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular