Homeዜናና ወቅታዊዜናበጎዳናዎች ላይ ወደ እስልምና በመጣራት የሚታወቀው ወንድም ፈቂህ ገለቶ ዋዬ በ50 ዓመት...

በጎዳናዎች ላይ ወደ እስልምና በመጣራት የሚታወቀው ወንድም ፈቂህ ገለቶ ዋዬ በ50 ዓመት ዕድሜው ወደ አኺራ ተሻገረ

በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ጎዳናዎች ላይ ወደ እስልምና በመጣራት የሚታወቀው ወንድም ፈቂህ ገለቶ ዋዬ ወደ አኺራ መሻገሩ የተሰማው ትናንት ማክሰኞ ግንቦት 6/2016 ነው፡፡ ወንድም ፈቂህ ሕይወቱ ያለፈው በሻሸመኔ ከተማ ሲሆን ሕልፈቱ ድንገተኛ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

ወንድም ፈቂህ ላለፉት 23 ዓመታት አዲስ አበባን ጨምሮ በኦሮሚያ፣ አማራ እና ሲዳማ ክልል የተለያዩ ከተሞች በአደባባይ ወደ እስልምና በመጣራት በሥፋት የሚታወቅ ነው፡፡ ወንድም ፈቂህ በሰኔ/2014 ከሚንበር ቲቪ “የኔ መንገድ” ፕሮግራም ጋር በነበረው ቆይታ የአደባባይ የዳዕዋ ሥራው ትዳሩን እንዳሳጣው ተናግሮ ነበር፡፡

ወንድም ፈቂህ ገለቶ ዋዬ፣ በአዲስ አበባ እና የክልል ከተሞች በሚያደርገው የዳዕዋ ሥራ እስር እና ድብደባ ሲያስተናግድ እንደቆየም ተናግሯል፡፡ ወንድም ፈቂህ ወደ እስልምና መጣራቱ ለእስር በሚዳርገው ጊዚ ጭምር ሥራውን በመቀጠል የተለያዩ ግለሰቦች ወደ እስልምና እንዲመለሱ ሰበብ መሆኑን ገልጧል፡፡

የቀድሞው ወታደር ፈቂህ ገለቶ፣ ወደ አኺራ የተሻገረው በ50 ዓመት ዕድሜው ነው፡፡ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በሻሸመኔ ከተማ በሚገኝ የሙስሊም መካነ መቃብር ትናንት ተፈጽሟል።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular