እሑድ , ربيع الأول 5, 1446
Google search engine
Homeዜናና ወቅታዊዜናስር የሰደደ ሕመም ያለባቸው ሑጃጆች የሕክምና ሠነድ መያዝ እንዳይዘነጉ ሳዑዲ ዐረቢያ አሳሰበች

ስር የሰደደ ሕመም ያለባቸው ሑጃጆች የሕክምና ሠነድ መያዝ እንዳይዘነጉ ሳዑዲ ዐረቢያ አሳሰበች

ለ1445ኛ ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ከመላው ዓለም ምዕመናንን እየተቀበለች የምትገኘው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ ስር የሰደደ ሕመም ያለባቸው ሑጃጆች የሕክምና ታሪካቸው የሠፈረበት ሠነድ መያዝ እንዳይዘነጉ አሳሰበች። ለዘንድሮው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ወደ ሀገሪቱ የገባ የባንግላዴሽ ዜግነት ያለው ምዕመን በዛሬው እለት መዲና ከተማ ውስጥ ኅልፈቱ ተሰምቷል።

የሳዑዲ ዐረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር ስር በሰደደ ሕመም ያለባቸው ምዕመናን የሕክምና ታሪካቸውን የሠፈረበት ሠነድ መያዝ እንዳይዘነጉ ያለው ድንገተኛ ሕመም ቢያጋጥማቸው የሕክምና ድጋፍ ለመስጠት እንዲያግዝ መሆኑን ገልጿል።

ለዓመታዊው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ የሚያመሩ ምዕመን ከጤናቸው ጋር ተያይዞ የኮቪድ19ና ሌሎች ክትባቶችን መውሰድ እንደሚኖርባቸው ቀደም ብሎ ተነግሯል።

በዘንድሮው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ላይ 12 ሺሕ ምዕመናንን በምትልከው ኢትዮጵያም፣ ከምዝገባ አንስቶ መስተንግዶውን በሚሰጠው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኩል የሕክምና ድጋፍ ሰጪ ቡድን መቋቋሙ ይፋ ተደርጓል።

የምክር ቤቱ የሐጅ እና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዐብዱልፈታህ መሐመድ በዘንድሮው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ኢትዮጵያዊያኑ ምዕመናን ድንገተኛ የጤና እክል ቢገጥማቸው የሕክምና ድጋፍ ሊሰጥ የሚችል ቡድን ማዋቀሩን ለሚንበር ቲቪ አረጋግጠዋል።

እንደ አቶ ዐብዱልፈታህ ከሆነ ምዕመናኑ 45 ግለሰቦችን በያዘ አንድ ቡድን ተደልድለዋል። እነዚህ ምዕመናን ድንገተኛ የጤና እክል ቢገጥማቸው የሕክምና ባለሞያዎች በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ ዝግጅት ተደርጓል። እንደ አቶ ዐብዱልፈታህ ከሆነ ምዕመናኑ 45 ግለሰቦችን በያዘ አንድ ቡድን ተደልድለዋል። እነዚህ ምዕመናን ድንገተኛ የጤና እክል ቢገጥማቸው የሕክምና ባለሞያዎች በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ ዝግጅት ተደርጓል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የባንግላዴሽ ዜግነት ያለው ለሐጅ የተጓዘ ምዕመን ሕይወት ማለፉን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ረቡዕ ዕለት በድንገት ተዝለፍልፎ መወደቁ የተነገረው የባንግላዴሽ ዜና የኅልፈት ዜና ይፋ የተደረገው ዛሬ ቅዳሜ ነው።

የዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ሰኔ 7/2016 ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። በመላው ዓለም የሚገኙ ወደ 2 ሚሊዮን ገደማ የሚቆጠሩ ምዕመናን ሥነ ሥርዐቱን ለመፈፀም ከግንቦት 1/2016 ጀምሮ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ መግባት ጀምረዋል። [ሚንበር ቲቪ]

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular