Homeዜናና ወቅታዊዜናለ“ቢላሉል ሐበሺ ሙዝየም” እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን የከተማው ባህል ኪነ ጥበብ እና...

ለ“ቢላሉል ሐበሺ ሙዝየም” እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን የከተማው ባህል ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ

የአዲስ አበባ የባህል ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ በከተማው የሚገኘው “ቢላሉል ሐበሺ ሙዝየም” እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ሙዝየሙ አሁን ካለበት የተሻለ ሠፊ ቦታ የሚገባው መሆኑን ጥቆማ ሰጥተዋል፡፡

የከተማው የባህል ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት፣ ቢላሉል ሐበሺ ሙዝየም በርካታ እስላማዊ ቅርሶችን የያዘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ምክትል ኃላፊው ለ”ኢትዮጵያን ቢዝነስ ሪቪው” መጽሔት ሲናገሩ፤ ቢሯቸው ሙዝየሙ ከሚሰጠው ጠቀሜታ አንጻር ድጋፍ ያስፈልገዋል የሚል እምነት እንዳለው በመግለጽ፣ ለዚህ እንዲረዳ የሚጠበቅበትን እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አያይዘው ጠቅሰዋል፡፡

የባህል ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊው፣ በቢሮው ቀጥታ የበጀት ድጋፍ ማድረግ ስለማይቻል ድጋፉ ሙዝየሙ የተሻለ ቦታ ላይ እንዲያርፍ ለሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት ጥያቄ ማቅረብ እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡ ሆኖም ከዚሁ ጉዳይ ጋር ተያይዞ እስካሁን ድረስ ከሙዝየሙ ይፋዊ ጥያቄ አልቀረበም ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የቢላሉል ሐበሺ ሙዝየም ተከፍቶ ለጎብኚዎች አገልግሎት መስጠት የጀመረው በ2010 ነው፡፡ ሙዝየሙ በተለይ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተበትነው የሚገኙ እስላማዊ ቅርሶችን ሰብስቦ የያዘ ነው፡፡ ሙዝየሙን በ2013 የጎበኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ በከተማው ሊጎበኙ ከሚገባቸው ቦታዎች አንዱ ነው ብለው ነበር፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular