Homeዜናና ወቅታዊዜናየጥቅምት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 14.6 በመቶ ሆኖ ተመዘገበ

የጥቅምት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 14.6 በመቶ ሆኖ ተመዘገበ

የጥቅምት ወር 2019 አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 14.6 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል። አገልግሎቱ ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 25/ 2019 ባወጣው መረጃ፣ የተያዘው ወር የዋጋ ግሽበት በጥቅምት 2018 ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ጭማሪ አሳይቷል።

ይሁን እንጂ በመስከረም ወር ከነበረው 14.9 በመቶ አንጻር መጠነኛ ቅናሽ አለው። የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ 14.1 በመቶ የጨመሩ ሲሆን በዋናነት ማር እና ቸኮሌት 36.2 በመቶ፣ ሥጋ 23.8 በመቶ ወተት፣ የወተት ተዋፅኦዎች እና እንቁላል 20.1 በመቶ እንዲሁም ዘይት እና ቅቤ 20.6 በመቶ ስኳር ጭማሪ በማስመዝገባቸው ጭማሪው ማሳየቱን አገልግሎቱ ገልጿል።

እንዲሁም አትክልት እና ፍራፍሬ እያንዳንዳቸው 11.1 በመቶ፣ ዳቦ እና እንጀራ 10.7 በመቶ፣ የምግብ ምርቶች 15.1 በመቶ መጨመራቸውንም አስታውቋል። በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 15.4 በመቶ የደረሰ ሲሆን ትራንስፖርት 17.1 በመቶ፣ አልኮል መጠጦችና ትምባሆ 18.92 በመቶ፣ በኮሙዩኒኬሸን 9.1 በመቶ ፣ ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች 11.1 በመቶ ጭማሪ አስመዝግበዋል። በተጨማሪም ትምህርት 15.5 በመቶ ፣ ጤና 10.5 በመቶ እና ሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች 19.1 በመቶ ሆነው ተመዝግበዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ጥቅምት 24፤ 2019 ባወጣው መግለጫ የዋጋ ግሽበት ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት “በድርብ አሃዝ” ውስጥ ይቆያል ተብሎ እንደሚጠበቅ ማስታወቁ ይታወሳል። ማዕከላዊ ባንኩ ለምግብ ነክ የዋጋ ግሽበት ዕድገት “ከፍተኛ አስተዋጽኦ” አድርገዋል ብሎ ከጠቀሳቸው ውስጥ የዳቦ፣ የእህል፣ የአትክልት የጥራጥሬ ምርቶች እና የቡና ዋጋ መጨመር ነው።

የኤሌክትሪክ ታሪፍ፣ የኬሮሲን እና የማገዶ እንጨት ዋጋ መጨመር ደግሞ ምግብ ነክ ላልሆኑ ዕቃዎች የዋጋ ግሽበት ዕድገት ምክንያት ተብለው ተዘርዘረዋል። ለታየው የዋጋ ግሽበት ዋነኛው ምክንያት፤ ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሳቢያ “ከአቅርቦት ጋር የተያያዘ” እንደሆነም ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ገልጿል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular