የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 17/2019 ባካሄደው ጨረታ፤ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ159 ነጥብ 70 ብር አማካይ ዋጋ እንደተሸጠ ይፋ ባደረገው የውጤት መግለጫ አሳውቋል፡፡ በዚህ የዶላር ጨረታ ከተሳተፉ 30 ባንኮች መካከል 28 የጠየቁትን ማግኘት ችለዋል፡፡ የዛሬው ኣማካይ ዋጋ ከዚህ ቀደም ከተሸጠበት 160 ነጥብ 10 ቅናሽ የታየበት ነው፡፡
ማዕከላዊ ባንኩ በዛሬው እለት የ140 ሚሊዮን ዶላር ለጨረታ ያቀረበ ቢሆንም የገበያው ፍላጎት 150 ሚሊዮን ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል። በጨረታው ለአንድ ዶላር የቀረበው ዝቅተኛ ተመን 158 ነጥብ 18 ብር በዶላር ሲሆን፣ ከፍተኛው ደግሞ 160 ነጥብ 99 ብር ሆኖ ተመዝግቧል። (ሚንበር ቲቪ)












