Homeዜናና ወቅታዊዜናየማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ምዝገባ በመዲናዋ ተጀመረ

የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ምዝገባ በመዲናዋ ተጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ፤ የመዲናዋ ነዋሪዎች ከጥቅምት 1 እስከ ኅዳር 30/2019 በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ምዝገባ እንደሚካሄድ አስታውቋል፡፡ ቢሮው በ2019 በጀት ዓመት ከ3 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ፤ የጤና መድኅን ተጠቃሚዎች የነባር አባላት ዕድሳትና የአዲስ አባላት ምዝገባን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት በርካታ የከተማዋን ነዋሪዎች በማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

በ2018 በጀት ዓመት ከ2 ነጥብ 75 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አባል የሆኑ ሲሆን፤ ከ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ አባላትና ቤተሰቦቻቸው ከጤና ጣቢያ ጀምሮ ባሉት የመንግሥት ጤና ተቋማት የሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በ2019 የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ነባር አባላት ሙሉ በሙሉ ዕድሳታቸውን እንዲያካሂዱና ከ10 በመቶ በላይ አዲስ አባላትን በመመዝገብ በአጠቃላይ ከ3 ሚሊዮን በላይ የመዲናዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል።

መክፈል የሚችሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች አቅማቸውን ያገናዘበ ዓመታዊ መዋጮ በመክፈል የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አባል እንደሚሆኑ የገለፁት የቢሮ ኃላፊው፤ የመክፈል አቅም የሌላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ በጀት ተይዞ ዓመታዊ ክፍያቸው እንደሚሸፈን ገልጸዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በ2019 ዓ.ም ለማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አባላት ዓመታዊ መዋጮ 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ድጎማ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

ኅብረተሰቡ ራሱንና ቤተሰቡን ካልታሰበ የሕክምና ድንገተኛ ወጪ ለመጠበቅ የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አባል መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።

የከተማ አስርተዳደሩ ካጸደቃቸው መካከል፤ የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን፣ ማኅበረሰብ አቀፍና የማኅበራዊ ጤና መድኅን ሥርዓቶችን መሠረት አድርጎ የሚሠራ ነው፡፡ የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ሥርዓት በኢ- መደበኛ ኢኮኖሚ የሚሠሩ ወይም መደበኛ ደመወዝና ገቢ የሌላቸው ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፣ ሁለተኛው ማኅበራዊ የጤና መድኅን ግን በመደበኛ ክፍለ ኢኮኖሚ የተሠማሩትን ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ሥርዓት ነው፡፡

የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ሥርዓት የሙከራ ትግበራውን የጀመረው በ2013 በሦስት ወረዳዎች ነበር። በመላ ኢትዮጵያ የጤና መድኅን ምዝገባና ዕድሳት የሚከናወነው በየዓመቱ ከመስከረም 1 እስከ የካቲት 30 ቀን ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular