Homeዜናና ወቅታዊዜናየኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን በእስራኤል ባለሥልጣናት ትዕዛዝ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን በእስራኤል ባለሥልጣናት ትዕዛዝ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ተደረገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን በእስራኤል ባለሥልጣናት ትዕዛዝ በበረራ ላይ እያለ ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዲመለስ መደረጉ ተገልጿል። የጭነት አውሮፕላኑ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ የተደረገው ዜግነቱ ኢንዶኔዥያዊ የሆነ አብራሪ መካተቱ መረጋገጡን ተከትሎ ነው። 

እንደ አናዶሉ ዘገባ ከሆነ፣ ሰኞ ጥቅምት 2/2019 አውሮፕላኑ ከአዲስ አበባ ከተነሳ በኋላ የተሳፋሪዎችና የሠራተኞች ዝርዝር ለእስራኤል ባለሥልጣናት እንደተላከ ተገልጿል። በዚህም እስራኤል ከኢንዶኔዥያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደሌላት በመጥቀስ ወደ እስራኤል የአየር ክልል እንዳይገባ ከልክላለች። በዚህ ምክንያት አውሮፕላኑ በበረራው ወቅት የጫነውን ነዳጃ ወደ ባሕር ከደፋ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል፡፡

ይሁን እንጂ የካርጎ አውሮፕላኑ አብራሪ የነበረው ኢንዶኔዥያዊ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ ወደ ቴል አቪቭ ለመግባት ፈቃድ ባለው ሌላ አብራሪ እንዲተካ ተደርጓል፡፡ በዘገባው መሠረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪው ወደ እስራኤል እንዳይገባ መከልከሉን አለማወቁን በመጥቀስ ድርጊቱ ስህተት እንደነበር አስታውቋል።

የእስራኤል ባለሥልጣናት የውጭ አየር መንገዶች ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከሌላቸው የተወሰኑ ሀገራት የመጡ የሠራተኞች አባላትን ወደ ሀገሪቱ በሚሄዱ በረራዎች ላይ እንዳይመድቡ መመሪያ መስጠታቸው ተገልጿል።

ከእነዚህ ሀገራት ውስጥ የኢንዶኔዥያ፣ አፍጋኒስታን፣ አልጄሪያ፣ ኢራን፣ ኢራቅ፣ ኩዌት፣ ኒጀር፣ ኳታር፣ ሳዑዲ ዐረቢያ፣ ሶማሊያ እና የቬንዙዌላ ዜጎች ተካተዋል። በጉዳዩ ዙርያ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ሆነ የኢንዶኔዥያ መንግሥት ማብራሪያ አልሰጡም።

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን በኤክስ ገጽ ላይ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስራኤሉ አቻቸው ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በዋና ዋና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን አብራርተዋል፡፡ በውይይቱ በጋራ ጉዳዮች ላይ ያለንን ትብብር ለማጠናከር ያለንን ቁርጠኝነትም አረጋግጠናል ብለዋል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular