Homeዜናና ወቅታዊዜናየቱሉ ካፒ የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት ወደ ግንባታ ምዕራፍ መሸጋገሩን የኬፊ ጎልድ ኤንድ...

የቱሉ ካፒ የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት ወደ ግንባታ ምዕራፍ መሸጋገሩን የኬፊ ጎልድ ኤንድ ኮፐር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘውና በ330 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነባው የቱሉ ካፒ የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት፤ ወደ ግንባታ ምዕራፍ መሸጋገሩን ማይኒንግ ሪቪው አፍሪካ የኬፊ ጎልድ ኤንድ ኮፐር ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

በዓመት በአማካይ 166 ሺሕ ወቄት ወርቅ ያመርታል ተብሎ የሚጠበቀው ኬፊ ጎልድ ኤንድ ኮፐር፤ ‘የቱሉ ካፒ’ የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት በጸጥታ እና ጂኦፖለቲካዊ ቀውሶች ምክንያት ከ6 እስከ 7 ዓመታት ገደማ ተጓትቷል ሲሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ሃሪ አናኖስታራስ አዳምስ ገልጸዋል።

ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከተመደበለት ፕሮጄክት ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት 20 ሚሊዮን ዶላር በማዋጣት የ17 በመቶ ድርሻ ይዟል ተብሏል። ማዕድን ማውጣቱ ክፍት እና ከመሬት በታች የማውጣት ዘዴዎችን አጣምሮ የሚጠቀም ሲሆን በ2020 መገባደጃ ላይ ሥራ ጀምሮ በ2021 ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

የቱሉ ካፒ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ የስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት ነው ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ሃሪ አናኖስታራስ-አዳምስ፤ በቀጣዩ አስር ዓመት የማዕድን ዘርፉ ለሀገሪቱ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በአሁኑ ወቅት ካለበት 1 በመቶ ወደ 10 በመቶ ከፍ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ዋናውን ሚና ይጫወታል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

እንደዘገባው ከሆነ ፕሮጄክቱ እ.ኤ.አ በ2013 ኬፊ 75 በመቶ ድርሻውን ከኒዮታ ሚነራልስ የገዛው ቢሆንም በ2014 የቀረውን ድርሻ በመግዛት የፕሮጀክቱን 100 በመቶ ባለቤትነት ተቆጣጥሯል። በ2015 በወቅቱ ዝቅተኛ በነበረው የወርቅ ዋጋ መሠረት የተሻሻለ የአካባቢና የኢኮኖሚ ጥናት ከተካሄደ በኋላ የማዕድን ማውጣት ፈቃድ ተሰጥቶታል። ይሁን እንጂ ባለፉት ዓመታት በነበሩት የጸጥታና የጂኦፖለቲካዊ ቀውሶች እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ አለማግኘት ለፕሮጄክቱ መዘግየት ምክንያት መሆናቸው ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዐት የገንዘብ ድጋፉ ሙሉ በሙሉ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ፕሮጀክቱ በመንግሥትና በግል ኢንቨስተሮች ትብብር የሚሠራ መሆኑን በመጥቀስ “የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክት የተፈጥሮ ኃብታችንን እንዴት ለሀገር እና ሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚያሳይ ዐይነተኛ አብነት ነው” ሲሉ ገልጸውት ነበር፡፡

ቱሉ ካፒ በምዕራብ ኢትዮጵያ ውስጥ በመልማት ላይ ከሚገኙት ሁለት ትላልቅ የወርቅ ፕሮጀክቶች አንዱ ነው፡፡ በአካባቢው ሌላኛው ተጠቃሽ ኩርሙክ የተሰኘው ፕሮጀክት ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular