Homeዜናና ወቅታዊዜናየዑምራ ተጓዦች ሳዑዲ ዐረቢያን ለቅቀው የሚወጡበት የመጨረሻ ቀን ይፋ ተደረገ

የዑምራ ተጓዦች ሳዑዲ ዐረቢያን ለቅቀው የሚወጡበት የመጨረሻ ቀን ይፋ ተደረገ

ሳዑዲ ዐረቢያ በዑምራ ቪዛ ወደ ሀገሯ የገቡ ምዕመናን ለቅቀው የሚወጡበትን የመጨረሻ ቀን አሳውቃለች፡፡ የሀገሪቱ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ መሠረት፤ የዑምራ ቪዛ የያዙ ምዕመናን ከዙልቀዕዳህ 1/1447 ዓ.ሂ ማለትም ሚያዝያ 10/2018 በፊት ለቅቀው መውጣት ይኖርባቸዋል፡፡  

በተቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ ሀገሪቱን ለቅቀው መውጣት ያልቻሉ ምዕመናን እስራት እና የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠበቃቸው ያስታወቀው ሚኒስቴሩ፤ ጊዜ አሳልፈው ለሚቀመጡ ሰዎች የትራንስፖርት እና መጠለያን ጨምሮ ማንኛውንም አገልግሎት ለሚሰጡ የሳዑዲ ዜጎች እና ነዋሪዎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡ ይህን ማስጠንቀቂያ የተላለፈ ማንኛውም የሳዑዲ ዜግነት የሌለው ነዋሪ ደግሞ ከሀገር መባረርን ጨምሮ ጥብቅ ቅጣት ይጠብቀዋል ተብሏል፡፡

ሚኒስቴሩ የሳዑዲ ዐረቢያን የኢሚግሬሽን እና የሐጅ ደንቦችን ለማስከበር ክትትሉን እንደሚቀጥል በማሳወቅ፤ በአጥፊዎች ላይ ርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል። የዑምራ አገልግሎት ሰጪዎችም የቪዛ ገደብ ያለፈባቸው የዑምራ ተጓዦች ካሉ ወዲያውኑ ሪፖርት እንዲያደርጉ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት መመሪያ ሰጥተዋል። አገለግሎቱ ሰጪዎቹ ይህን መፈጸመማቸው ከቅጣት እንዲጠበቁ ያደርጋቸዋል ሲል አሳስቧል፡፡

በዑምራ ቪዛ የገቡ ምዕመናን ለቅቀው የሚወጡበትን የጊዜ ሠሌዳ ያስቀመጠችው ሳዑዲ ዐረቢያ፤ በቀጣይ ከመላው ዓለም የሐጅ ሥነ ሥርዐት ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡ ምዕመናንን ማስተናገድ ትጀምራለች፡፡ የዘንድሮው ሐጅ የሚከናወነው ከግንቦት 16 እስከ ግንቦት 21/218 ነው፡፡ እነዚህ ቀናት በሂጅሪ የዘመን ቀመር ከዙልሒጃ 8 እስከ 13/1447 ይውላሉ፡፡ ቀናቱ በወሩ መጨረሻ ቀናት የጨረቃ መታየት ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular