Homeዜናና ወቅታዊዜናየኢንዶኔዥያ መንግሥት በመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት ሳቢያ ለሐጅ ጉዞ የአደጋ ጊዜ እቅዶችን እያዘጋጀ...

የኢንዶኔዥያ መንግሥት በመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት ሳቢያ ለሐጅ ጉዞ የአደጋ ጊዜ እቅዶችን እያዘጋጀ መሆኑን ገለጸ

የኢንዶኔዥያ መንግሥት በመካከለኛው ምሥራቅ እየተባባሰ የመጣው ግጭት የበረራ መስመሮችን ሥጋት ላይ በመጣሉ፤ ለዘንድሮው የሐጅ ጉዞ የጥንቃቄ ርምጃዎችንና አማራጭ እቅዶችን እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል። የሀገሪቱ የሐጅ እና ዑምራ ጉዳዮች ሚኒስቴር የመንግሥት ዋነኛ ትኩረት የዜጎችን ደኅንነት ማረጋገጥ ነው ብሏል፡፡ ለዚህም ሁኔታዎችን እየገመገመ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ይህ የመጣው እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ፤ ኢራን ሳዑዲ ዐረቢያን ጨምሮ በባሕረ ሰላጤው ሀገሮች አጸፋ ሰጥታ ግጭቱ በመስፋፋቱ ነው። ተባብሶ የቀጠለው የሀገራቱ ጦርነት 14ኛ ቀኑን ይዟል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተጓዦችን ደኅንነት ለማስጠበቅ አማራጭ ብሎ ካስቀመጣቸው መንገዶች አንደኛው መደበኛው የበረራ መስመር አደገኛ ሆኖ ከተገኘ የበረራ መስመር መቀየር ነው። ለዚህም ሲባል በአፍሪካ አሕጉር በኩል አልፎ የሚሄድ ረዥም ግን ደግሞ ደኅንነቱ የተጠበቀ አማራጭ መስመር ለመጠቀም ሐሳብ አቅርቧል። የበረራ መስመሮች በመቀየራቸው ምክንያት ሊመጣ የሚችለውን የዋጋ ጭማሪን ለመቋቋም የሚያስችል የፋይናንስ እቅድ ማውጣትንም እንደ አማራጭ አስቀምጧል። የግጭቱ ሁኔታ እየተባባሰ የሚሄድ ከሆነ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የሐጅ ጉዞውን የመነሻ ቀን ሊያራዝም እንደሚችልም አስታውቋል። 

እስካሁን ባለው እቅድ መሠረት በኢንዶኔዥያ የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ መርሃ ግብር የመጀመርያ የሐጅ ተጓዦች ቡድን በሚያዝያ 14/2018 ጉዞውን እንደሚጀምር ይጠበቃል። ይሁን እንጂ መንግሥት በቀጣዮቹ ቀናት የግጭቱን ሁኔታ እየገመገመ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ገልጿል። ለዘንድሮው ሐጅ ወደ 221 ሺሕ ገደማ የኢንዶኔዥያ ምዕመናን ተሳታፊ እንደሚሆኑ ጃካርታ ግሎብ ዘግቧል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular