Homeዜናና ወቅታዊዜናታንዛንያ ለእስላማዊ የባንክ አገልግሎት አዲስ የሕግ ማዕቀፍ አስተዋወቀች

ታንዛንያ ለእስላማዊ የባንክ አገልግሎት አዲስ የሕግ ማዕቀፍ አስተዋወቀች

የታንዛንያ ማዕከላዊ ባንክ ባንክ ኦፍ ታንዛንያ፤ ለእስላማዊ የባንክ አገለግሎት እና ወለድ አልባ የባንክ አገለግሎት በመስኮት ለሚሰጡ አጠቃላይ የሕግ ማዕቀፍ ይፋ አድርጓል። ደንቡ የፍቃድ አሰጣጥ፣ የአስተዳደር፣ የሸሪዓ ተገዢነት መርሆዎችን፣ የፋይናንስ አወቃቀር እና ያልተፈቀዱ ገቢዎችን አያያዝ ያካተተ ነው።

በአዲሱ ደንብ መሠረት፤ በእስላማዊ ባንክ አገልግሎት ሰጪነት ሥራ የሚጀምር የሚጀምር ማንኛውም አካል፤ ግብይትም ሆነ የአሠራር ሥርዐቱን ጨምሮ ሁሉም አገልግሎቶቹ ከሸሪዓ መርሆዎች ጋር ሙሉ በሙሉ የሚጣጣም መሆኑን እንዲያሳይ ይጠበቅበታል። ከወለድ ነጻ የባንክ አገለልግሎትን በመስኮት ደረጃ ለማስጀመር የሚፈልጉ መደበኛ ባንኮችም በቅድሚያ ከታንዛንያ ማዕከላዊ ባንክ የብቃት ማረጋገጫ ማግኘት እንደሚኖርባቸው ተገልጿል፡፡ ባንኮቹ የአስተዳደር ሥርዐቱን፣ የሒሳብ አያያዝ ፖሊሲዎችን፣ የሠራተኞችን ቁጥር፣ ገንዘቡን ወለድ ላይ ከተመሠረቱ እንቅስቃሴዎች መለየቱን የሚያሳይ የአዋጭነት ጥናት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡  

የእስላማዊ ባንክ አገልግሎት የሚሰጥ እያንዳንዱ ተቋም የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ ማቋቋም እንደሚኖርበትም ተደንግጓል፡፡ ኮሚቴው ለቦርዱ በሸሪዓ ጉዳዮች ላይ ምክር ለመለገሥ፣ አገልግሎቶችን ለመገምገም እና ለማፅደቅ፣ የሸሪዓ ኦዲት ግኝቶችን ለመገምገም፣ ተቀባይነት የሌላቸውን ገቢዎች አያያዝን ለመቆጣጠር እና በየሩብ ዓመቱ ሪፖርቶችን ለቦርዱ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

የታንዛንያ መንግሥት ባለሥልጣናት አዲስ ይፋ ያደረጉትን እስላማዊ የባንክ አገልግሎት ደንብ ለማዘጋጀት ያለፉትን አምስት ዐመታት ሲሠሩ መቆየታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular