Homeዜናና ወቅታዊዜና“ትራምፕ ሀገሮች የጋዛን 'የሰላም ቦርድ' ለመቀላቀል አንድ ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍሉ ይፈልጋሉ” -...

“ትራምፕ ሀገሮች የጋዛን ‘የሰላም ቦርድ’ ለመቀላቀል አንድ ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍሉ ይፈልጋሉ” – ሪፖርት

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ “የሰላም ቦርድ” በመባል በሚጠራው ቡድን ውስጥ ለመቆየት ሀገሮች አንድ ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍሉ ይፈልጋሉ ሲል የዘገበው ብሉምበርግ ነው፡፡ ዋና መቀመጫውን በኒውዮርክ ያደረገው የዜና ምንጭ ተመለከትኩት ባለው የቡድኑ ረቂቅ ቻርተር፤ የመጀመርያ የሰላም ቦርድ ሊቀመንበር ራሳቸውን ያደረጉት ትራምፕ፣ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ይኖራቸዋል፡፡

ቻርተሩ በሥራ ላይ ከዋለ በመጀመርያው ዓመት ሀገሮች ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለሰላም ቦርድ በልገሣ ሰጥተው ካልሆነ በስተቀር፤ አባልነቱ የሚገደበው ለሦስት ዓመታት ብቻ ነው፡፡ ገንዘብ የሚያወጡ ከሆነ ግን “የቋሚ አባልነት” ዋስትና እንደሚሰጣቸው ሰነዱ ያረጋግጣል፡፡ ረቂቅ ቻርተሩ ያሰፈረው ይህ አንቀጽ “ትራምፕ ራሳቸው ከአባልነት ክፍያዎች የሚሰበሰቡትን ገንዘብ” እንደሚቆጣጠሩ ጠቋሚ ሆኖ ተወስዷል፡፡

የቻርተሩ መግቢያ “የሰላምን ግንባታ የሚከታተል ይበልጥ ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ ዓለም አቀፍ አካል” እንደሚያስፈልግ በመግለጽ፤ ዘላቂ ሰላም ለማግኘት “ብዙ ጊዜ [ተሞክረው] ከከሸፉ ተቋማት ለመራቅ የሚያስችል ድፍረት” እንደሚያስፈልግ አስፍሯል፡፡ ሚድል ኢስት ዐይ እንደዘገበው፤ ይህ ትራምፕ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ላይ “ባላንጣ ለመፍጠር ሙከራ እያደረጉ ነው” የሚል ሥጋት እንዲፈጠር አድርጓል።

ባለፈው ሣምንት መጨረሻ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር እና የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ ማርኮ ሩቢዮን የሰላም ቦርድ በሚል ሥያሜ ላቋቋሙት አካል አባል በማድረግ አካተዋል። ክትራምፕ በታች የቦርዱ ዋና ሰው ይሆናሉ የተባሉት ብሌር ናቸው፡፡ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ፣ የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ እና የፕሬዝዳንቱ አማች ያሬድ ኩሽነርም ተካተዋል። የእለት ተዕለት ስትራቴጂ መንደፍ እና ኦፕሬሽኖችን በበላይነት ለመቆጣጠር ሁለት ከፍተኛ አማካሪዎችም ተሠይመዋል። ቡልጋሪያዊው የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት የመካከለኛው ምሥራቅ የሰላም አስተባባሪ ኒኮላይ ማላዴኖቭ የጋዛ ከፍተኛ ተወካይ ሆነው ያገለግላሉ።

ከሀገሮች መካከል የግብፅ፣ የቱርክ፣ የአርጀንቲና እና የካናዳ መሪዎች ቦርዱን እንዲቀላቀሉ ግብዣ እንደቀረበላቸው ተናግረዋል። ብሉምበርግ ከእነዚህ በተጨማሪ በርካታ የአውሮፓ ሀገሮችም ግብዣ ቀርቦላቸዋል ብሏል፡፡ የአልባኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኤዲ ራማ፣ የብራዚሉ ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ፣ የቆጵሮሱ ፕሬዚዳንት ኒኮስ ክሪስቶዱሊዲስ፣ የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን፣ የጣሊያን ጆርጂያ ሜሎኒ እና የሮማኒያው ፕሬዚዳንት ኒኩሶር ዳንም እንዲሁ ግብዣከቀረበላቸው ውስጥ እንደሚገኙበት ኤኤፍፒ ዘግቧል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular