Homeዜናና ወቅታዊዜናሊቢያ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ጨምሮ 39 ስደተኞችን ማባረሯን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገለጹ

ሊቢያ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ጨምሮ 39 ስደተኞችን ማባረሯን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገለጹ

የሊቢያ ባለሥልጣናት ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ጨምሮ 39 መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞችን መባረራቸውን የገለጹት “ሕገ ወጥ ስደትን ለመቆጣጠር እና የድንበር ደኅንነትን ለማስከበር” ተወስዷል ባሉት ርምጃ ነው፡፡ ርምጃው ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ የግብፅ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ ዜጎች ያካተተ ነው፡፡

በሁለት ቡድን ተከፍለው ተልከዋል ከተባሉት ስደተኞች መካከል የግብፅ ዜጎች በኤምሳዐድ ድንበር አቋርጠው ወደ ሀገራቸው ገብተዋል። የኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኤርትራ ስደተኞችን የያዘው ቡድን ደግሞ ቤንጋዚ ወደሚገኘው ቀንፉዳ የተሠኘ ማጎሪያ እንዲዘዋወሩ ከተደረገ በኋላ መላካቸው ተገልጿል። ይሁን እንጂ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ስለ ኢትዮጵያውያኑ መመለስ እስካሁን ድረስ ያወታው መረጃ የለም፡፡

በማዕከሉ የሚገኙ አንድ ከፍተኛ የኤጀንሲ ባለሥልጣን፤ “በሊቢያ ሕጋዊ ፍቃድ የሌላቸው ሰዎች የማስወጣት ሒደቱን እያጠናቀቅን ነው” ማለታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡ ሊቢያ በተለይም በሜድትራንያን ባሕር በኩል ወደ አውሮፓ ለመሻገር በሚፍልሱ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ ስደተኞች ዋና የመተላለፊያ ሀገር ሆና ቆይታለች።

በተጠናቀቀው የአውሮፓውያን ዐመት፤ ከ700 በላይ ሱዳናውያን እና ከ1 ሺሕ 100 በላይ ግብፃውያን ከምሥራቅ ሊቢያ መባረራቸውን ሪፖርቶች ያመለክታሉ። የዓለም አቀፉ የፍልሠተኞች ድርጅት ሊቢያ ለስደተኞች ማረፊያነት አደገኛዋ መዳረሻ መሆኗን ይገልጻል።

የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብዱልሐሚድ ዲቤይባህል፤ “ሊቢያ መደበኛ ላልሆነ ፍልሥት መዳረሻ አትሆንም” ሲሉ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፍልሰትን በመቆጣጠር ረገድ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።                                                            የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) እና የዓለም አቀፍ የፍልሰተኝች ድርጅት  (IOM) በጋራ ባወጡት ሪፖርት፤ እ.አ.አ በ2024 ከ 127 ሺሕ በላይ ስደተኞች የሜድትራኒያን ባህርን ለማቋረጥ ሙከራ ማድረጋቸውን ይገልጻል።

አይኦኤም በተጠናቀቀው 2025 ከነሐሴ እስከ ጥቅምት ድረስ የ44 የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ያላቸው 929 ሺሕ ስደተኞች ወደ ሃገሪቱ መግባታቸውን በሪፖርቱ ላይ አስፍሯል። ከእነዚህ መካከል ከ1 ሺሕ 200 በላይ ኢትዮጵያውያን ዜጎች እንደሚገኙበት ተገልጿል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular