Homeዜናና ወቅታዊዜናሳዑዲ ዐረቢያ ከኢስላም ሕግጋት ጋር የሚጣረሱ ሥያሜዎች ለሕዝብ መገልገያዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ...

ሳዑዲ ዐረቢያ ከኢስላም ሕግጋት ጋር የሚጣረሱ ሥያሜዎች ለሕዝብ መገልገያዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አገደች

ቅዱሳኑን ከተሞች ያቀፈችው ሳዑዲ ዐረቢያ፤ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የሕዝብ መገልገያዎች ከኢስላም ሕግጋት ጋር ተስማሚ ሥያሜዎችን እንዲይዙ የሚያስገድድ አዳዲስ ደንቦችን ይፋ አድርጋለች። በኦፊሴላዊው ዑሙል ቁራ ጋዜጣ የታተመው አዲሱ ደንብ፤ ማንኛውም መስጂድ፣ ትምሕርት ቤት፣ ሆስፒታል ወይም የመንግሥት ሕንጻ ሥያሜ ሙሉ በሙሉ ከኢስላም ሕግና አስተምሕሮ ጋር የሚስማማ መሆን እንዳለበት ያደነግጋል፡፡

በሥም አሰጣጥ ደንቡ ውስጥ ከተካተቱ ቁልፍ እስላማዊ ድንጋጌዎች መካከል ሁሉም ሥያሜዎች ከኢስላም አስተምሕሮ እና መርሆዎች ጋር እንዲስማሙ ከማድረግ በተጨማሪ፤ የአላህ (ሱ.ወ) ሥሞች (አስማኡል ሑስና) በሥያሜነት አገልግሎት ላይ ሲውሉ በሰባት ብቻ እንዲገቡ ያዝዛል፡፡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተፈቀዱት አስ-ሰላም (የሰላም ምንጭ)፣ አል-ዐድል (ፍትሕ ራሱ)፣ አል-አወል (የመጀመሪያው)፣ አን-ኑር (ብርሃን)፣ አል-ሐቅ (እውነታው)፣ አሽ-ሸሂድ (መስካሪው፤ ከእርሱ ምንም የማይሰወር) እና አል-መሊክ (ንጉሡ፤ ሉዓላዊው ጌታ፤ ፍጹም ግዛት ያለው፣ ግዛቱም ከማንኛውም ጉድለት የጸዳ የሆነ) የሚሉት ብቻ ናቸው፡፡

ከአላህ (ሱ.ወ) ሥሞች በተጨማሪ የንጉሣዊ እና የአመራር ሥሞችን በሚመለከት፤ የሀገሪቱ ንጉሥ ቀጥተኛ ፍቃድ ካልሰጡ በስተቀር ተቋማት በነገሥታት፣ ዘውድ ላይ በተቀመጡ ልዑላን ወይም በውጭ ሀገሮች መሪዎች ሥም ሊጠሩ እንደማይችል ክልከላ ተቀምጧል፡፡

ታትሞ ከተሠራጨ ከ120 ቀናት በኋላ ተግባራዊ የሚደረገው ደንብ፤ መስጂዶች፣ የትምህርት ተቋማት፣ የባሕል ማዕከላት እና የትራንስፖርት መሠረተ ልማቶችን ጨምሮ በሁሉም የሕዝብ ባለቤትነት በተያዙ ተቋማት ላይ ተፈጻሚ ይደረጋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular