Homeዜናና ወቅታዊዜናውይይትን በጥብቅ የሚቃወሙ የግብፅ ባለሥልጣናት ተደጋጋሚ ዛቻ የሀገሪቱ መንግሥት የ21ኛውን ክፍለ ዘመን...

ውይይትን በጥብቅ የሚቃወሙ የግብፅ ባለሥልጣናት ተደጋጋሚ ዛቻ የሀገሪቱ መንግሥት የ21ኛውን ክፍለ ዘመን እውነታ ለመቀበል አለመቻሉን ማሳያ ነው – የኢትዮጵያ መንግሥት

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ውይይትን በጥብቅ የሚቃወሙ የግብፅ ባለሥልጣናት ተደጋጋሚ ዛቻ የሀገሪቱ መንግሥት የ21ኛውን ክፍለ ዘመን እውነታዎች ለመቀበል አለመቻሉን ማሳያ መሆናቸውን በመግለጽ ድርጊቱን ነቅፏል። ሚኒስቴሩ ዛሬ ረቡዕ ኅዳር 24/2018 ባወጣው መግለጫ፣ የግብጽ ባለሥልጣናት የንግግር ቅኝት የተመሠረተው በቅኝ ግዛት ዘመን አስተሳሰብ መሆኑን በመጥቀስ ኋላ የቀረ መሆኑን አስታውቋል።

በዚህ ቅኝት የዐባይ ውሃ ሙሉ በሙሉ በእነሱ እጅ እንደሆነ ይሰማቸዋል ያለው መግለጫው፤ ከዚህ መላቀቅ እንደሚገባም አስገንዝቧል። የባለሥልጣናቱ ድርጊት ባለፉት ጊዜያት ግብጽ በድርድር ሒደት ውስጥ ያለች በማስመሰል የመፍትሔ መንገዶች ትዘጋ እንደነበር በመግለጽ፣ አሁን ግን ትርጉም ባለው ውይይት ለመሳተፍ ፍቃደኛ አለመሆኗን ፍንትው ብሎ መታየቱን ጠቁሟል።

ኢትዮጵያ የዐባይን ወንዝ በመጠቀም የአሁኑን እና ቀጣዩን ትውልድ ፍላጎት ለማሟላት የመጠቀም መብቷን በፍትሐዊነት መርሆዎች ላይ በመመርኮዝ፤ ለሁሉም ጠቃሚ የሚሆኑ የመፍትሔ አማራጮችን ለመፈለግ በሯ ክፍት መሆኑን መንግሥት በድጋሚ አረጋግጧል።

የመንግሥት መግለጫ የመጣው፤  የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በድር ዓብዱልአጢ፣ ሀገራቸው በሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት እና አስተዳደር ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ተጨማሪ ንግግር እንደማታካሄድ ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ በሠጡት ቃለ ምልልስ መናገራቸውን ተከትሎ ነው።

ከሕዳሴ ግድቡ ምርቃት በኋላ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት ይበልጥ መሻከሩን የገለጹት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በጉዳዩ ዙሪያ ሥጋት ሊሠማው ይገባል ብለዋል። ግድቡ ከዓለም ቀፍ ሕግ ውጭ የተወሰደ የተናጥል ርምጃ እንደሆነም በመናገር፣ ኢትዮጵያ ግብጽን ሳታማክር ወስዳለች ላሉት ርምጃ ዕውቅና አንሰጥም ብለዋል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular