Homeዜናና ወቅታዊዜናሳዑዲ ዐረቢያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ1 ሺሕ 600 በላይ ሰዎች ድንበር ጥሰው ወደ...

ሳዑዲ ዐረቢያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ1 ሺሕ 600 በላይ ሰዎች ድንበር ጥሰው ወደ ሀገሯ ሊገቡ ሲሉ በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቀች

የሳዑዲ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር፤ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ ለመግባት ሲሞክሩ ነበሩ ያለቻቸውን 1 ሺሕ 667 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ የኢትዮጵያውያን ዜጎች ቁጥር 57 በመቶ መሆኑን የሚኒስቴሩ ሪፖርት ያመለክታል፡፡

ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ 42 በመቶ የመናውያን እንዲሁም ቀሪው ከሌሎች ሀገሮች የተነሱ ናቸው፡፡ በተጨማሪም 31 ሰዎች በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገሪቱ ለመውጣት ሲሞክሩ መያዛቸውንም አክሏል።

በተያያዘ የሳዑዲ የጸጥታ ባለሥልጣናት ባለፈው ሣምንት 21 ሺሕ 134 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገልጸዋል። ገልፍ ኒውስ እንደዘገበው ከሆነ፤ የሀገሪቱ ርምጃ በሀገር አቀፍ ደረጃ የነዋሪነት፣ የድንበር እና የሠራተኛ ጥሰቶች ላይ አነጣጥሯል የተባለው ዘመቻ አካል መሆኑን የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል። ከበርካታ የመንግሥት ኤጀንሲዎች ጋር በመቀናጀት ተደርጓል የተባለው ዘመቻ፤ ከኅዳር 11 እስከ ኅዳር 27/2018 ባሉት ቀናት ውስጥ የተካሄደ ነው። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል 13 ሺሕ 128 የነዋሪነት፣ 4 ሺሕ 826 ደግሞ የድንበር ደኅንነት ደንቦችን ጥሰዋል ተብሏል። እንዲሁም 3 ሺሕ 180 ሰዎች የሠራተኛ ሕጎችን በመጣስ ለእስር የመዳረጋቸው ምክንያት ተጠቅሷል፡፡

ባለሥልጣናቱ እንዳሉት የ22 ሺሕ 71 ግለሰቦች የጉዞ ሠነዶቻቸውን ለማግኘት ወደ ዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖቻቸው ልከዋል፡፡ 5 ሺሕ 78 ደግሞ የጉዞ ዝግጅቶቻቸው እንዲጠናቀቅ ተልከዋል፡፡ በተመሳሳይ ወቅት 11,674 ሰዎች ከሀገር እንዲባረሩ መደረጉንም ጨምረው ተናግረዋል። ሳዑዲ በአጠቃላይ 31 ሺሕ 91 የውጭ ዜጎች ማለትም 29 ሺሕ 538 ወንዶች እና 1 ሺሕ 553 ሴቶች ጉዳያቸው ሕጋዊ ሂደት ተከትሎ እየታየ መሆኑ ተገልጿል።

የሳዑዲ የውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሕገ ወጥ ተግባር ላይ መጠለያ፣ መጓጓዣ ወይም የትኛውም ዐይነት ድጋፍ የሚያደርግ ማንኛውም ሰው እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስራት ወይም እስከ አንድ ሚሊዮን የሳዑዲ ሪያል ቅጣት እንደሚጠብቀው አስጠንቅቋል። ጥቅም ላይ የዋሉ ተሽከርካሪዎችን ወይም ንብረቶችን ሊወርስ እንደሚችል አክሏል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular