Homeዜናና ወቅታዊዜናአዲስ አበባ 32ኛውን የአየር ንብረት ጉባዔ ለማስተናገድ ተመረጠች

አዲስ አበባ 32ኛውን የአየር ንብረት ጉባዔ ለማስተናገድ ተመረጠች

ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2027 የሚካሄደውን የኮፕ32 የአየር ንብረት ጉባኤ አስተናጋጅ በመሆን መመረጧ ዛሬ ማክሰኞ ይረጋገጣል ሲሉ የዘንድሮው የኮፕ30 ጉባኤ ፕሬዝዳንት ነግረውኛል ብሎ ሬውተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡ ጉባኤው በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ሀገሮች በመርህ ደረጃ የተስማሙት በብራዚል እየተካሄደ በሚገኘው የኮፕ30 ስብሰባ የመጀመሪያ ቀን ውሎ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ አንድሬ ኮሬያ ዶ ላጎ ተናግረዋል።

ይሁንና ኢትዮጵያ መመረጧ በይፋ ማረጋገጫ የሚያገኘው ዛሬ ማክሰኞ ይሆናል ተብሎ እንደሚጥዕበቅ ጥቆማ ሰጥተዋል፡፡ በዘገባው መሠረት፤ ኢትዮጵያ ጉባኤውን ለማስተናገድ ማመልከቻ ያስገባችው በመስከረም ወር ነበር፡፡ ናይጄሪያ በተመሳሳይ ጉባኤውን ለማስተናገድ ጥያቄ ብታቀርብም፤ የአፍሪካ ሀገራሮች ቢሮ በአንድ ድምፅ ኢትዮጵያ የአስተናጋጅነት እጩ እንድትሆን ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የዘንድሮ ዐመት የኮፕ30 የአየር ንብረት ጉባኤ በአሁኑ ሰዐት እየተካሄደ የሚገኘው በብራዚል ቤሌም ነው። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular