Homeዜናና ወቅታዊዜናሳዑዲ ዐረቢያ ከቀጣዩ ሣምንት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ አዲስ የዑምራ ቪዛ ደንብ ይፋ...

ሳዑዲ ዐረቢያ ከቀጣዩ ሣምንት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ አዲስ የዑምራ ቪዛ ደንብ ይፋ አደረገች

ሳዑዲ ዐረቢያ በዑምራ ሥነ ሥርዐት ላይ ለመሳተፍ ከመላው ዓለም የሚጓዙ ምዕመናን የሦስት ወር የዑምራ ቪዛ ቢሰጣቸውም፤ በአንድ ወር ውስጥ ዕድሉን ተጠቅመው ወድ ቅዱሳኑ ከተሞች ካልተጓዙ እንደሚሠረዝ አስታውቃለች፡፡ ሀገሪቱ ይህን የደንብ ማሻሻያ ይፋ ያደረገችው፤ በሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር አማካይነት ነው፡፡

አል ዐረቢያ የሚኒስቴሩን ምንጮች በመጥቀስ እንደዘገበው፤ ሀገሪቱ ቪዛውን ያገኙ ምእመናን በአንድ ወር ጊዜ እንዲገቡ አስገዳጅ ሕግ ብታወጣም፤ ሳዑዲ አረቢያ ከገቡ በኋላ መቆየት የሚችሉበትን የሦስት ወር ጊዜ ላይ የአሠራር ለውጥ አላደረገችም፡፡ አዲሱ ደንብ ከቀጣዩ ሣምንት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

በሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ መሠረት፤ አዲሱ የዑምራ ወቅት ከጀመረበት ሰኔ ወር መጀመሪያ አንስቶ ከመላው አለም የዑምራ ቪዛ  የተሰጣቸው ምዕመናን ቁጥር ከአራት ሚሊዮን በላይ ደርሷል። በዚህ ዓመት የዑምራ ወቅት በአምስት ወራት ውስጥ ብቻ ከቀዳሚዎቹ ወቅቶች ጋር ሲነፃፀር የውጭ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular