Homeዜናና ወቅታዊዜናየዘካ ሥርዐት ለማኅበራዊ ዋስትና የሚኖረውን አስተዋጽኦ ለመጨመር ሥርዐት ሊበጅለት ይገባል ተባለ

የዘካ ሥርዐት ለማኅበራዊ ዋስትና የሚኖረውን አስተዋጽኦ ለመጨመር ሥርዐት ሊበጅለት ይገባል ተባለ

የዘካ ሥርዐት ለማኅበራዊ ደኅንነት የሚኖረውን አስተዋጽኦ ለመጨመር ሥርዐት ሊበጅለት ይገባል ያሉት፤ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሑሪያ ዓሊ ናቸው፡፡ ወይዘሮ ሑሪያ ይህን የተናገሩት፤ ጥቅምት 13/2018 ሕብረት ባንክ ከደንበኞች የሰበሰበውን 35 ሚሊዮን ብር ለ10 ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጋፍ ባደረገበት መድረክ ነው

በዚሁ ንግግር ላይ የባንክ ተቋማት ለኢኮኖሚው ከሚያበረክቱት በተጨማሪ ከሀገር አቀፍ የማኅበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና የአሠራር ማዕቀፍ ጋር በተናበበ መንገድ መሥራት እንደሚኖርባቸው ጠቁመዋል፡፡

ሚኒስትር ዲኤታዋ ከዚህ ጋር አያይዘው ባነሱት የዘካ ሥርዐት፤ የማኅበራዊ ደኅንነት ጥበቃን ለማጠናከርና ሚናው አሁን ካለው በላቀ ደረጃ እንዲጎለብት ለማስቻል በትብብር መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ መሥሪያ ቤታቸው ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዘካ ኮሚሽን ጋር መሥራት እንደሚፈልግም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ የዘካ እና የአውቃፍ ኮሚሽን መመሥረቱን ያስታወቀው በሰኔ 2017 ነበር፡፡ በወቅቱ የዘካ ኮሚሽን ቦርድ፣ የአውቃፍ ኮሚሽን ቦርድ እና የዘካ እና የአውቃፍ ኮሚሽን የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ሰይሟል፡፡ ይሁን እንጂ ቦርዱ እስካሁን ያከናወናቸውን ሥራዎች በተመለከተ የተገለጸ ነገር የለም፡፡ (ሚንበር ቲቪ

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular