Homeዜናና ወቅታዊዜናበቢሾፍቱ ለሚገነባው አየር ማረፊያ ግንባታ አራት የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገሮች የልማት የፋይናንስ ተቋማትን...

በቢሾፍቱ ለሚገነባው አየር ማረፊያ ግንባታ አራት የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገሮች የልማት የፋይናንስ ተቋማትን “የማግባባት ሥራ መሠራቱን” አቶ አሕመድ ሽዴ ተናገሩ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚያስገነባው አየር ማረፊያ ግንባታ፤ አራት የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገሮች የልማት የፋይናንስ ተቋማትን የማግባባት ሥራ መሠራቱን የገንዘብ ሚኒስተሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተናገሩት፤ የዓለም ባንክ ግሩፕ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ዓመታዊ ስብሰባዎችን ማጠቃለያ በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ነው፡፡ ሚኒስትሩ የመሩት ልዑክ የተሳተፈበት ስብሰባ የተደረገው በአሜሪካ ዋሺንግተን ነው፡፡

አቶ አሕመድ በመግለጫው እንደተናገሩት፤ “የሳዑዲ ዐረቢያ የልማት ፈንድ”፣ “የኳታር የልማት ፈንድ”፣ “የአቡዳቢ የልማት ፈንድ” እና “የኩዌት የልማት ፈንድ”፤ አዲሱን አየር ማረፊያ ፋይናንስ እንዲያደርጉ “የማግባባት ሥራ” ተሠርቷል፡፡ ሚኒስትሩ ይህን ሥራ “በተሳካ ሁኔታ ተፈጽሟል” ብለዋል፡፡ ከእነዚህ ሀገሮች በተጨማሪም የአሜሪካ፣ አውሮፓ እና እስያ ተቋማትንም የማግባባት ሥራ እንደተሠራ ቢናገሩም የሀገሮቹን ዝርዝር አልጠቀሱም፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥት ተጨማሪ ፋይናንስ እየተፈለገለት ለሚገኘው አየር ማረፊያ፤ የግንባታው ባለቤት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ ቀደም ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ለአዲሱ አየር መንገድ ግንባታ የሚውል የ7 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራርሟል። ከአራት ዓመታት በኋላ ይጠናቀቃል የተባለው አየር ማረፊያው፤ በአፍሪካ ቀዳሚ እንደሚሆን በኅላፊዎች ተገልጿል።

አየር ማረፊያው ሲጠናቀቅ በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ስኩዌር ሜትር ላይ የሚያርፍ የመንገደኞች ተርሚናል፣ 126 ሺሕ190 ስኩዌር ሜትር ላይ የሚያርፍ ለአየር መንገዱ ድጋፍ የሚሰጡ ተቋማት እና 100 ሺሕ ስኩዌር ሜትር ላይ የሚያርፍ የጭነት አገልግሎት መስጫ ያካትታል። በቢሾፍቱ የሚገነባው ይህ አየር ማረፊያ በአዲስ አበባ ከሚገኘው የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጋር በፈጣን መንገድ እንዲሁም በፈጣን ባቡር እንደሚገናኝም ተገልጿል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular