Homeዜናና ወቅታዊዜናበአዲስ አበባ ከተማ የ2018 የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ምዝገባ ተጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ የ2018 የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ምዝገባ ተጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የ2018 የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ምዝገባ መጀመሩን በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ፤ ምዝገባው ከጥቅምት 1 እስከ ኅዳር 30/2018 እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡  

እንደ ኃላፊው ከሆነ፤ የነባር አባላት መዋጮ ስሌት ዝቅተኛው 1 ሺሕ 500 ብር፣ ከፍተኛው 10 ሺሕ 500 ብር እና የመመዝገቢያ 200 ብር በአጠቃላይ በየደረጃቸው ተደምሮ ይከፈላል፡፡ በአጠቃላይ በገቢ እርከን ደረጃ የክፍያ መጠን በጣም ከፍተኛ 10 ሺሕ 500 ብር፣ ከፍተኛ 6 ሺሕ 900 ብር፣ መካከለኛ 2 ሺሕ ብር፣ ዝቅተኛ 1 ሺሕ 500 እንዲሁም በጣም ዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች መንግሥት ይሸፈንላቸዋል፡፡ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ልጆች እና በአባሉ ጥላ ስር ለሚኖሩ ተጨማሪ ቤተሰቦች የመሠረታዊ ቤተሰቡ 50 በመቶ መዋጮ እንደሚከፈል አክለዋል፡፡

በከተማው ጤና ቢሮ መረጃ መሠረት፤ በ2017 ከ2 ሚሊዮን 500 ሺሕ ዜጎች በላይ በማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አባልነት ታቅፈዋል፡፡

ዓመታት ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ጤና መድኅን አገልግሎት፣ የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን፣ ማኅበረሰብ አቀፍና የማኅበራዊ ጤና መድኅን ሥርዓቶችን መሠረት አድርጎ የሚሠራ ነው፡፡ የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ሥርዓት በኢ- መደበኛ ኢኮኖሚ የሚሠሩ ወይም መደበኛ ደመወዝና ገቢ የሌላቸው ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፣ ሁለተኛው ማኅበራዊ የጤና መድኅን ግን በመደበኛ ክፍለ ኢኮኖሚ የተሠማሩትን ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ሥርዓት ነው፡፡

የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ሥርዓት የሙከራ ትግበራውን የጀመረው በ2013 በሦስት ወረዳዎች ነበር። በመላ ኢትዮጵያ የጤና መድኅን ምዝገባና ዕድሳት የሚከናወነው በየዓመቱ ከመስከረም 1 እስከ የካቲት 30 ቀን ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ ነው፡፡ በእነዚህ ወራት እያንዳንዱ ወረዳ ኅብረተሰቡ ገቢ ያገኝባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን ሁለት ወራት መርጦ ምዝገባና ዕድሳት እንዲያካሄድ ያደርጋል፡፡ በዚህ መልኩ የሚከናወነው ምዝገባና ዕድሳት የካቲት 30 ቀን መጠናቀቅ እንደሚኖርበት የኢትዮጵያ ጤና መድኅን አገልግሎት መረጃ ያመለክታል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular