Homeዜናና ወቅታዊዜናየትራምፕ ወኪሎችንና የሐማስ ተደራዳሪዎችን ከመጋረጃ ጀርባ ለ40 ደቂቃ ያፋጠጠው ውይይት

የትራምፕ ወኪሎችንና የሐማስ ተደራዳሪዎችን ከመጋረጃ ጀርባ ለ40 ደቂቃ ያፋጠጠው ውይይት

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡት ባለ 20 ነጥብ የጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነት በሐማስ እና እስራኤል መካከል ተቀባይነት ማግኘቱ ከተገለጸ በኋላ፤ በመጀመሪያ ምእራፍ 20 ምርኮኞች ሲለቅቁ፣ በምትኩ ፍልስጤማውያን ነጻ ወጥተዋል፡፡

ይህ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ትራምፕን በመወከል በሻርም አል ሸይኽ የተገኙት የመካከለኛው ምሥራቅ ልዩ ልዑኩ ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጃሬድ ኩሽነር፤ በካይሮ ከሐማስ ተደራዳሪዎች ጋር ለ40 ደቂቃ ፊት ለፊት ተገናኝተው መነጋገራቸውን አክሲዮስ አስነብቧል፡፡

ባለፈው ሣምንት የተካሄደው የዚህ ውይይት ሐሳብ አመንጪ የኳታር ባለሥልጣናት ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎ ዊትኮፍ እና ኩሽነር ከነበሩበት ቪላ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሌላ ቪላ በመሄድ የቱርክ እና የግብፅ የሥለላ ኃላፊዎች፣ ከፍተኛ የኳታር ባለሥልጣናት እና ከአራት ከፍተኛ የሃሐማስ መሪዎች ጋር ተገናኝተዋል፡፡ ሐማስ የተመራው በዋና ተደራዳሪው ኸሊል አል ሐያ አማካይነት ነው፡፡

በውይይቱ ላይ፤ ዊትኮፍ ለሐማስ አመራሮች በጋዛ ስለሚገኙ የእስራኤል ምርኮኞች በማንሳት “አሁን ጥቅም ከማስገኘት ይልቅ ለእናንተ እዳ ናቸው” በማለት፤ “የስምምነቱን የመጀመሪያ ምዕራፍ ለመቀጠል በሁለቱም ወገኖች ያሉትን ሰዎች ወደ ቤታቸው ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው” ብለዋል፡፡

በዚህ ወቅት የሐማሱ አል ሐያ፤ ትራምፕ ለሐማስ ልዑካን ቡድን ያስተላልፉት መልዕክት ይኖር እንደሆነ ለዊትኮፍ ባቀረቡት ጥያቄ፤ “የፕሬዝዳንቱ መልዕክት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ትስተናገዳላችሁ” የሚል መሆኑን በመጥቀስ፤ የቀረበው የሰላም እቅድ ነጥብ ሁሉም ነጥብ “እንዲተገበር አደርጋለሁ” ማለታቸውንም አንስተዋል፡፡ ይህን ተከትሎ በስብሰባው ማብቂያ ላይ የሐማስ መሪዎች ከግብጽ፣ ከኳታር እና ከቱርክ አደራዳሪዎች ጋር ወደ ተለየ ክፍል የሄዱ ሲሆን፣ የግብፅ የሥለላ ኅላፊ ሐሰን ረሻድ ከበርካታ ደቂቃዎች በኋላ ከቱርክ እና ከኳታር አቻዎቻቸው ጋር ተመልሰው ለዊትኮፍ እና ኩሽነር በነበረው ውይይት ላይ በመመርኮዝ “ስምምነት ላይ ደርሰናል” ሲሉ ነግረዋቸዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular