Homeዜናና ወቅታዊዜና“የነጃሺ 00” መንደር ፕሮጀክትን አጠቃላይ ሁኔታ የሚከታተል ቡድን ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ጋር...

“የነጃሺ 00” መንደር ፕሮጀክትን አጠቃላይ ሁኔታ የሚከታተል ቡድን ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ጋር ባንድነት እንደሰየመ ጠቅላይ ምር ቤቱ ገለጸ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ በትግራይ ክልል ውቅሮ የንጉሥ ነጃሺና የታላላቅ ሰሐባዎች የመቃብር ሥፍራ ያለበትን የነጃሺ 00 መንደር ፕሮጀክት “እውን ለማድረግ” ኤምባሲው ከዚህ ቀደም ያደርግ ነበር የተባለውን ትብብር “የሚያጠናክርበት ሁኔታ ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል” ሲል አሳውቋል፡፡ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች አምባሳደር መሐመድ ሳለም አል ረሽዲ ጋር በኤምባሲው በመገኘት መወያየታቸው ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ይህን ያስታወቀው ማክሰኞ መስከረም 20/2018 ባሠራጨው መረጃ ነው፡፡

በዚሁ ውይይት ላይ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጀምሮታል የተባለውን በትግራይ ክልል ውቅሮ የንጉሥ ነጃሺና የታላላቅ ሰሐባዎች የመቃብር ሥፍራ ያለበት “የነጃሺ 00 መንደር” ፕሮጀክት በጋራ እውን ለማድረግ እንዲረዳ አጠቃላይ ሁኔታውን ይከታተላል የተባለ ከሁለቱም ወገን የተውጣጣ ቡድን ተሰይሟል ተብሏል፡፡

በውይይቱ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የነጃሺ 00 መንደር ፕሮጀክት ቦርድ ሰብሳቢ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር አንዋር መሰጠፋ፣ የነጃሺ 00 መንደር ፕሮጀክት ቦርድ አባል ፕሮፌሰር አደም ካሚል፣ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እንዲሁም የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ሐሰን መሐመድሳለህ እንደተገኙም ተገልጿል፡፡

ለታላቁ የኢትዮጵያ ንጉሥ አል ነጃሺ መታሰቢያ ይሆናል የተባለው “የአል ነጃሺ 00 መንደር” ምሥረታ ንቅናቄ፣ ይፋ የተደረገው ሚያዝያ 29/2016 ነበር፡፡ በወቅቱ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደው የንቅናቄ መርሐ ግብር ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመንደር ምሥረታውን ተነሳሽነት መውሰዱ ተገልጿል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular