Homeዜናና ወቅታዊዜናዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳና አውስትራሊያ ለፍልስጤም ሀገርነት በይፋ ዕውቅና ሰጡ

ዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳና አውስትራሊያ ለፍልስጤም ሀገርነት በይፋ ዕውቅና ሰጡ

ዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳና አውስትራሊያ ለፍልስጤም ሀገርነት በይፋ ዕውቅና መስጠታቸውን ያስታወቁት ዛሬ እሑድ ነው። ታሪካዊ ነው የተባለው የሀገሮቹ ውሳኔ የተሰማው በኒውዮርክ ከሚጀምረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ አስቀድሞ ነው።

ከሀገሮቹ መካከል የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር በሐምሌ ወር እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነትን ማድረግ፣ የሁለት ሀገር መፍትሔ የሚያመጣ ዘላቂ ሰላም ማስፈን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የርዳታ አቅርቦቱን እንደገና እንዲጀምር መፍቀድን ጨምሮ፣ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ካልቻለች ሀገሪቱ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለፍልስጤም ዕውቅና ትሰጣለች ብለው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ከገለጹ ከሣምንታት በኋላ ዛሬ ባሠራጩት የቪድዮ መልዕክት የሰላምን እና የሁለት ሀገር መፍትሔን እንዲያንሠራራ የዚህ ታላቅ ሀገር ጠቅላይ ሚኒስትር እንደመሆኔ መጠን፣ ዩናይትድ ኪንግደም የፍልስጤምን ግዛት በይፋ ዕውቅና መስጠቷን በይፋ አሳውቃለሁ ብለዋል። ውሳኔው በብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ መሠረታዊ ለውጥ ነው መባሉን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

የእነ ዩናይትድ ኪንግደም ውሳኔ ይፋ ከተደረገ በኋላ የፈረንሳይ ርምጃ ይቀጥላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚድል ኢስት ዐይ ዘግቧል። ባለፈው ዓመት በተመሣሣይ ስፔን፣ አየርላንድ እና ኖርዌይ ዕውቅና ሰጥተዋል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular