የቱርክ ፕሬዝዳንት ረጀፕ ጠይብ ኤርዶጋን፤ ሙስሊሞች በምሥራቅ ቁድስ ላይ ያላቸውን መብት በፍጹም እንደማይተዉ በመግለጽ የእስራኤልን ጥቃት ለሚጋፈጡ ፍልስጤማውያን የሚሰጡትን ድጋፍ እንደሚቀጠሉ ተናግረዋል፡፡
ቱርክ በ1967 ድንበር ላይ የተመሠረት ምሥራቅ ቁድስ ዋና ከተማዋ ያደረገ ነፃ የፍልስጤም መንግሥት እንዲመሠረት ግፊት ማድረጓን እንደምትቀጥልም ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም በእስራኤል ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ስር ራሳቸውን ለማትረፍ እየታገሉ ላሉት የጋዛ ጭቁን ሕዝቦች ከጎናቸው ከመቆም ማንም ሊያግደን አይችልም ብለዋል።
እንደ ቅዱሳኑ መካ እና መዲና ከተሞች ሁሉ ቁድስም ለሙስሊሞች ቅዱስ ሥፍራ መሆኑን የገልጹት ኤርዶጋን፤ ይህ ሥፍራ “ቅዱስ ባልሆኑ እጆች እንዲቆሽሽ አንፈቅድም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በቀጣናው ውስጥ አለመረጋጋትን እያቀጣጠሉ ነው ተችተዋል፡፡ “በጭቆናና በዘር ማጥፋት የንጹሐን ሕፃናትን ሕይወት በመንጠቅ ደኅንነቱ የተጠበቀ የወደፊት ሕይወት መገንባት እንደሚችሉ የሚያምኑ ሰዎች ባፈሰሱት ደም ይወሰዳል” ሲሉ የንጹሐን ደም ፈስሶ እንደማይቀር ገልጸዋል፡፡
ቱርክ ዛሬም ሆነ ነገ ቀጣናውን ወደ ደም ባህር ለመቀየር የሚፈልጉ ሰዎችነ ትታገላለች ያሉ ሲሆን፤ በሶሪያ፣ በየመን፣ በሊባኖስ እና በኳታር በእስራኤል ጥቃት የተጠቁት ወገኖችን እንደሚደግፍ ተናግረዋል። (ሚንበር ቲቪ)












