Homeዜናና ወቅታዊዜናየብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ ሥልጣን ለቀቁ

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ ሥልጣን ለቀቁ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ከጥር 2015 አንስቶ ሲመሩ የቆዩት አቶ ማሞ ምሕረቱ፤ ሥልጣን መልቀቃቸውን ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 28/2017 ገልጸዋል፡፡ ገዥው ይህን የገለጹት በኤክስ ገጽ ላይ ባሠፈሩት የሥንብት መልዕክት ነው፡፡

ሰባት ዓመታት በተለያዩ የሕዝብ አገልግሎት መቆየታቸውን ያስታወሱት አቶ ማሞ፤ “የመንግሥት ሥልጣን ለመልቀቅ ጊዜው ደርሷል” ብለዋል፡፡ ገዥው በመልዕክታቸው “በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሠራነው ሥራ እጅግ በጣም ኩራት ይሰማኛል” በማለት አሥፍረዋል፡፡ በዚህ ቆይታ “ለሀገሪቱ እጅግ በጣም አስፈላጊ” ሲሉ የጠቀሱትን የኢኮኖሚ ማሻሻያ መምራታቸውን አስታውሰዋል፡፡ ይህን ዕድል ሰጥተውኛል ላሏቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

ተሰናባቹ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ምሥጋና ባቀረቡላቸው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት አስተዳደር የመጀመርያውን ሥልጣን ያገኙት በነሐሴ 2010 ነበር። አቶ ማሞ ምሕረቱ 10ኛው የብሔራዊ ባንክ ገዥ ነበሩ፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular