Homeዜናና ወቅታዊዜናማሌዥያ ዓለም አቀፍ የቁርኣን “ኢጃዛ” መድረክ አስተናገደች

ማሌዥያ ዓለም አቀፍ የቁርኣን “ኢጃዛ” መድረክ አስተናገደች

የማሌዥያ መዲና ኳላላምፑር የደቡብ ምሥራቅ እስያ ማኅበር አባል ሀገሮችን (ASEAN) ያሳተፈ ዓለም አቀፍ የቁርኣን ኢጃዛ አሰጣጥ መድረክ አስተናግዳለች፡፡ በመድረኩ ላይ ከአባል ሀገሮች የተውጣጡ የቁርኣን ኢጃዛ በመስጠት የተመከረላቸው ሊቃውንት ተሳታፊ መሆናቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ብቃታቸውን ላስመሰከሩ በቁርኣን ጥናት ለቆዩ ተማሪዎች በእነዚህ ሊቃውንት በቁርኣን ንባብ የተካኑ መሆናቸውን ማረጋገጫ ተሰጥቷል፡፡ ዐረብ ኒውስ እንደዘገበው፤ በዝግጅቱ ላይ ከደቡብ ምሥራቅ እስያ ሀገሮች የመጡ የእስልምና ሊቃውንት በተጨማሪ በሁለቱም ጾታ በሺሕዎች የሚቆጠሩ በቁርኣን ጥናት ያለፉ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

መድረኩን ያዘጋጀው መቀመጫን ሳዑዲ ዐረቢያ መካ ከተማ ያደረገው ሙስሊም ወርልድ ሊግ መሆኑ ታውቋል፡፡ ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ እንዳሳወቀው፤ የመድረኩ ዓላማ በቁርኣን ኢጃዛ ሒደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ እና ተግባራዊ መፍትሔዎችን ማቅረብ ነው፡፡

የቁርኣን ኢጃዛ አንድ ተማሪ ቁርኣንን የንባብ ሕግጋት እና ደንቦችን በጠበቀ መልኩ በቃሉ ማስታወስ መቻሉን የሚያረጋግጥ መምሕር ለተማሪ የሚሰጠው የምሥክር ወረቀት ነው። ቁርኣንን ሙሉ ለሙሉ በሒፍዝ ባያጠናቅቁም ሕግጋትን ጠብቀው ማንበባቸው ከተረጋገጠ ለተማሪው ሊሰጥ እንደሚችል ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ የኢጃዛ አሰጣጥ ሒደት የሰጪ እና ተቀባዩን የግንኙነት ሰንሰለት እንዲጠብቅ ይደረጋል፡፡ በሒደቱ የተሳተፉትን እያንዳንዱን መምሕራን የሚለየው ሰንሰለት አጭር በሚሆንበት መጠን፤ የኢጃዛውን ተዓማኒነት ጠንካራ ያደርገዋል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular