Homeዜናና ወቅታዊዜናፊሊፒንስ እስላማዊ ባሕልን የሚያስተዋውቅ ሐላል የከተማ ማዕከል ልትመሠርት ነው

ፊሊፒንስ እስላማዊ ባሕልን የሚያስተዋውቅ ሐላል የከተማ ማዕከል ልትመሠርት ነው

በደቡብ ምሥራቅ እስያ ውስጥ የምትገኘው ፊሊፒንስ፤ እስላማዊ ባሕልን የሚያስተዋውቅ ሐላል የከተማ ማዕከል ልትመሠርት መሆኗን የዋና ከተማዋ ማኒላ ከንቲባ ኢስኮ ሞሬኖ ገልጸዋል፡፡ በሐላል ከተማው ማረጋገጫ የተሰጣቸው ሐላል ምግብ የሚያቀርቡ ሬስቶራንቶች፣ ቅርስ እንዲሁም ባሕልን የሚያጎሉ የቱሪስት መዳረሻዎች ይኖሩታል ተብሏል፡፡

የከተማው ምሥረታ ይፋ የተደረገው የሙስሊም ፊሊፒናውያን ብሔራዊ ኮሚሽን ከሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ካካሄዱ በኋላ ነው፡፡ በውይይቱ ላይ የማኒላ ከንቲባ ባሕላዊ ሐላል ምግብ አቅራቢዎች ትክክለኛ እና ጥራትን ለማረጋገጥ የምስክር ወረቀት ሥርዓት እንዲጀመር ሐሳብ አቅርበዋል፡፡ የከተማው ግንባታ ሲከናወን በማኒላ የመጀመሪያውን እስላማዊ የመቃብር ሥፍራ እና የሙስሊም አማካሪ ምክር ቤትን የሚያካትት ይሆናል፡፡

አዲሱ ፕሮጀክት የአካባቢውን ቱሪዝም እና ሙስሊም ነክ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎችን በማጎልበት ሃይማኖታዊ አካታችነትን እንደሚያሳድግ ባለሥልጣናት መናገራቸውን ኢስላሚክ ኢንፎርሜሽን ዘግቧል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular