Homeዜናና ወቅታዊዜናበደራሲ ማክዳ አርሺ የተዘጋጀው “Shining As I Am”፤ “እንዳለሁ አበራለሁ” በሚል ርእስ...

በደራሲ ማክዳ አርሺ የተዘጋጀው “Shining As I Am”፤ “እንዳለሁ አበራለሁ” በሚል ርእስ ወደ አማርኛ ተተርጎሞ ተመረቀ

ደራሲ ማክዳ አርሺ ያዘጋጀችው “Shining As I Am” የተሰኘው የሕፃናት መጽሐፍ፤ “እንዳለሁ አበራለሁ” በሚል ርእስ ወደ አማርኛ ተተርጎሞ ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 1/2017 በስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ ተመርቋል፡፡ በእውቁ ደራሲ ታገል ሠይፉ ወደ አማርኛ የተመለሰው መጽሐፍ ትኩረት፤ የአንጎል ዕድገት ውስንነት ተብለው ከሚታወቁ ሕመሞች መካከል አንደኛው በሆነው ኦቲዝም ላይ ነው፡፡

በመጽሐፉ አንድ ኦቲዝም ያለበት ሕፃን የአንድ ቀን ውሎ በራሱ አንደበት ይተርካል። ታሪኩ ሕፃናት የኦቲዝምን ምንነት በቀላልና በግልፅ ቋንቋ እንዲረዱ ከማስቻሉም በላይ፤ በልዩነት ውስጥ ያለውን ውበትና ጥንካሬ እንደሚያጎላ ተገልጿል፡፡

ደራሲ ማክዳ አርሺ በመጽሐፏ ኦቲስቲከ ልጆች ዓለምን የሚገነዘቡበት መንገድ ልዩ መሆኑንና ይህም እንደ እርግማን ወይም እብደት ሳይሆን እንደ ተፈጥሯዊ የአእምሮ እድገት ልዩነት ሊታይ እንደሚገባ አስረድታለች፡፡

በመጽሐፍ ምርቃት ሥነ ሥርዐቱ ላይ ደራሲ ማክዳ አርሺ፣ ደራሲ እና ገጣሚ ታገል ሠይፉን ጨምሮ ዕውቁ የእስልምና መምሕር ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ማክዳ አርሺ ከዚህ ቀደም ”የዓለም መብራቶች” የተሰኘ ሌላ የሕፃናት መፅሐፍ ለንባብ በማብቃት በሥራዎቿ በርካታ ሽልማቶችን እግኝታለች። “Shining As I Am” በአማዞን በርካታ ቅጂዎች የተሸጠ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular