Homeዜናና ወቅታዊዜናቦርዱ በአማራ እና ቤንሻንጉል ክልሎች የመራጭነት ምዝገባን በድጋሚ አራዘመ

ቦርዱ በአማራ እና ቤንሻንጉል ክልሎች የመራጭነት ምዝገባን በድጋሚ አራዘመ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ፤ በአማራ እና ቤንሻንጉል ክልሎች የምዝገባ ሒደት በድጋሚ መራዘሙን ያስታወቀው ዛሬ ጁመዓ ሐምሌ 25/2017 ነው። ቦርዱ ባሠራጨው መረጃ፣ የምርጫ ምዝገባ ሒደቱ ከነገ ቅዳሜ ሐምሌ 26/2017 እስከ ሐምሌ 30/2017 ድረስ ይቀጥላል።

ለምዝገባው መራዘም ካስቀመጣቸው ምክንያቶች መካከል “የአማራ ክልል የቆዳ ሥፋትና የሀሪማዎች ብዛት”፣ “የምርጫ ቁሳቁስ ሥርጭት በጊዜ አለመዳረስ”፣ “ወቅቱ የክረምት ጊዜ በመሆኑ በሁለቱም ክልሎች በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ምዝገባ ለማከናውን አለመቻላቸውን ተከትሎ የምርጫ አስፈፃሚዎች ለፈዴራል ምርጫ አስፈጻሚ አካል ተጨማሪ የምዝገባ ቀን እንዲጨመር መጠየቃቸው” ይገኝበታል።

የምርጫ አስፈፃሚ ቦርዱ በተመሣሣይ ሐምሌ 15/2017 ባወጣው መግለጫ፣ በምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ አለመግባባት ምዝገባ የተቋረጠ መሆኑ፣ የቁሳቁስ ሥርጭት በጊዜ ባለመዳረሱ እና በዚህ ሳቢያ የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ በወቅቱ አለመሰጠቱን በመግለጽ ምርጫውን ለተጨማሪ ቀናት አራዝሞ እንደነበር ይታወሳል። ቦርዱ በወቅቱ ለመራዘሙ በምክንያት ከዘረዘራቸው ውስጥ “የምርጫ ቁሳቁስ ሥርጭት በጊዜ አለመዳረሱን” በዛሬው መግለጫም በድጋሚ አቅርቧል።

የ2017 ምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ፤ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የመራጭነት ምዝገባ መጠናቀቁን የገለፀው ሐምሌ 13/2017 ነው። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular