የኢንዶኔዥያ መንግሥት በመካ ከተማ መስጂደል ሐረም አቅራቢያ፤ የሐጅ መንደር ለመገንባት መሬት ለመግዛት ሒደት መጀመሩን የሀገሪቱ ኢንቨስትመንት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፕራቦዎ ሲቢያንቶ አቅራቢነት በልዑል አልጋ ወራሽ ሙሐመድ ቢን ሰልማን መጽደቁ የተነገረው የኢንዶኔዥያ የሐጅ መንደር ዕቅድ፤ ሳዑዲ ዐረቢያ በመጪው ዓመት ጥር ወር ጀምሮ ተግባራዊ በምታደርገው የውጭ አካላትን የተንቀሳቃሽ ንብረት ባለቤትነትን በሚፈቅደው ሕግ ተፈጻሚ የሚደረግ ነው፡፡
የኢንዶኔዥያ ኢንቨስትመንት ሚኒስትር ሮሳን ሮስላኒ ለፕሬዝዳንቱ ባቀረቡት ሪፖርት መሠረት፤ የሳዑዲ ባለሥልጣናት ከ25 እስከ 80 ሔክታር የሚደርሱ ቦታዎችን በመስጂደል ሐረም አቅራቢያ ፈቅደዋል፡፡ በዚህ ስምምነት ኢንዶኔዥያ እስከ ጥቅምት ወር ድረስ ዝርዝር የመሠረተ ልማት ዲዛይን እና የልማት ዕቅዶችን ማቅረብ ይጠበቅባታል፡፡
አዲሱ መንደር ከመኖሪያ ቤት በተጨማሪ ዓመቱን ሙሉ ጎብኚዎችን የሚያገለግል የንግድ ሥፍራን እንደሚያካትት ጃካርታ ግሎብ ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡
ሳዑዲ ዐረቢያ ተግባራዊ በምታደርገው የውጭ ኩባንያዎችና ባለሐብቶች በሀገሪቱ ንብረት እንዲያፈሩ በሚፈቅደው ሕግ መሠረት፤ በመካ እና መዲና ፍቃድ የተሰጣቸው ሙስሊሞች ብቻ ናቸው፡፡ ሙስሊም ያልሆኑ ከመካ እና መዲና ውጪ ባሉት ሪያድ እና ጂዳ ከተሞች ተንቀሳቃሽ ያልሆነ ንብረት ማፍራት ይችላሉ፡፡ (ሚንበር ቲቪ)












