Homeዜናና ወቅታዊዜናየተኩስ አቁም ስምምነት የማይደረስ ከሆነ ለፍልስጤም ዕውቅና እንደሚሰጡ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ

የተኩስ አቁም ስምምነት የማይደረስ ከሆነ ለፍልስጤም ዕውቅና እንደሚሰጡ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ

የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር፤ እስራኤል በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የማትደርስ ከሆነ በመስከረም ወር ሀገራቸው ለፍልስጤም ሉዓላዊ ሀገርነት ዕውቅና እንደምትሰጥ ተናግረዋል። ስታርመር ይህን የተናገሩት አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ካደረጉ በኋላ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን በገለጹበት ወቅት በጋዛ የሚፈፀመውን ሰብዓዊ ቀውስ ለማስቆም ብቸኛው መንገድ ዘላቂ ስምምነት ነው ብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ አስተያየት የመጣው በጋዛ በተከሰተው ረሐብ ንጹሐን እየረገፉ መሆኑ በሚነገርበት ሰዓት ነው።

በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ጨምሮ በተያዘው ሣምንት ሁለት ታዋቂ የእስራኤል ድርጅቶችን ጨምሮ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች እስራኤል በጋዛ ላይ የፈፀመችው ጥቃት የዘር ማጥፋት ነው ሲሉ ፈርጀውታል። በተመሣሣይ በተያዘው ሐምሌ ወር በዩናይትድ ኪንግደም 60 ገደማ የብሪታንያ የፓርላማ አባላት ወደ እስራኤል የሚላኩ የጦር መሣሪያዎች ሙሉ በሙሉ እንዲታገዱ ጠይቀዋል።

ሚድል ኢስት ዐይ እንደዘገበው፣ ስታርመር የሀገራቸውን ዕቅድ ይፋ ከማድረጋቸው አስቀድሞ ሰኞ ዕለት ከቀናት በፊት ሌላኛዋ የአውሮፓ ሀገር ፈረንሣይ ዕውቅና እንደምትሰጥ ይፋ ማድረጓን ተከትሎ ተቃውሞ ካሰማችው ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ተገናኝተዋል።

በስኮትላንድ አበርዲን ውስጥ በተካሄደው ውይይት ላይ ለፍልስጤም መንግሥት ዕውቅና ለመስጠት ስለያዙት ዕቅድ ነግረዋቸዋል። የፈረንሣይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ ሀገራቸው በመስከረም ወር በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለፍልስጤም ሀገረ መንግሥት ዕውቅና እንደምትሰጥ ያሳወቁት ባለፈው ሣምንት መገባደጃ ነበር።

ፕሬዝዳንት ማክሮን ይህን ባስታወቁት የኤክስ ገጽ ጽሑፍ፣ በአሁኑ ሰዓት በጋዛ አንገብጋቢው ጉዳይ ጦርነቱን በማቆም “ለንጹሐን እፎይታ መስጠት ነው” ብለዋል፡፡ ማክሮን ለፍልስጤም ሀገረ መንግሥት ዕውቅና ለመስጠት አስቀድመው ዕቅድ ያስቀመጡት፤ ባለፈው ወር ሳይካሄድ በቀረው የተባበሩት መንግሥታት ጉባዔ ላይ ነበር፡፡

ከ193 የተባበሩት መንግሥታት አባል ሀገሮች መካከል ቢያንስ 142 የሚሆኑት በአሁኑ ወቅት ለፍልስጤምን ሉዓላዊ ሀገርነት ዕውቅና ሰጥተዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular