Homeዜናና ወቅታዊዜናሳዑዲ ዐረቢያ በትራምፕ የቀረበውን የጋዛ ነዋሪዎችን የማፈናቀል ዕቅድ ለማስቆም “የጎላ ሚና ተጫውታለች”...

ሳዑዲ ዐረቢያ በትራምፕ የቀረበውን የጋዛ ነዋሪዎችን የማፈናቀል ዕቅድ ለማስቆም “የጎላ ሚና ተጫውታለች” ተባለ

ሳዑዲ ዐረቢያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀርቦ የነበረውን የጋዛ ነዋሪዎችን በማፈናቀል ወደ ጎረቤት ሀገሮች የማዘዋወር ዕቅድ ለማስቆም፤ የጎላ ሚና መጫወቷን ዋላ የተሰኘ ድር ገጽን ጠቅሶ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡  

ድረ ገጹ የእስራኤል ምንጮችን በመጥቀስ ባወጣው ዘገባ እንዳመለከተው፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀደመ እቅዳቸውን የሠረዙት በሪያድ ከሳዑዲ ዐረቢያ ባለሥልጣናት ጋር “ስትራቴጂካዊ ስምምነቶችን ከተፈራረሙ በኋላ ነው”፡፡

በየካቲት ወር ይፋ ባደረጉትና የጋዛ ነዋሪዎችን ለማፈናቀል ይዘውት በነበረው እቅድ መሠረት፤ ፍልስጤማውያንን እንዲነሱ ካደረጉ በኋላ ሥፍራውን ወደ ቅንጡ ሪዞርት የመቀየር እቅድ እንደያዙ ተናግረው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እቅዱ በዐረቡ ዓለም እና በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከፍተኛ ውግዘት ገጥሞታል፡፡

በወቅቱ የጋዛ ነዋሪዎችን ለማፈናቀል ያቀረቡትን እቅድ ተከትሎ የዐረብ እና ሙስሊም ሀገሮች በሪያድ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ፤ የዐረብ ሊግ የጋዛን መልሶ ማልማት የተመለከተ ተለዋጭ እቅድ ለመውጣትም ተገዷል፡፡

ትራምፕ ለቅንጡ ሪዞርት በተመኙት ጋዛ የእስራኤል ጦር በቀጠለው ጥቃት፤ በአንድ ዓመት ከመንፈቅ ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ54 ሺሕ በላይ ንጹሐን ተገድለዋል፡፡ በከተማዋ የሚፈጸመውን ጥቃት ለማስቆም የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ባለፉት ሳምንታት በአሜሪካ የቀረበ ነው የተባለ የድርድር ሐሳብ ላይ የሐማስ እና የእስራኤል ባለሥልጣናት “ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ” በኳታር ዶሐ ውይይት ቢያደርጉም ከስምምነት ላይ ባለመደረሱ ለቀጣይ ሣምንት ሰኞ እንዲሻገር ተደርጓል፡፡

ለ60 ቀናት ይቆያል በተባለው በተኩስ አቁም ድርድሩ መሠረት፤ በእስራኤል ማጎሪያ ቤቶች የሚገኙ ፍልስጤማዊያን ነጻ ሲወጡ፤ በምትኩ በሐማስ እጅ የሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች ይለቀቃሉ መባሉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular