Homeዜናና ወቅታዊዜናየመጅሊስ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ለሁለት ሣምንት ተራዘመ

የመጅሊስ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ለሁለት ሣምንት ተራዘመ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ በ2017 ለሚያካሄደው የመጅሊስ ምርጫ፣ የመራጮችን የምዝገባ ጊዜ ለሁለት ሣምንት አራዝሟል። ቦርዱ ይህን የገለጸው ዛሬ እሑድ ሰኔ 29/2017 ለሁሉም ክልል ምርጫ ቦርድ አባላት በጻፈው ደብዳቤ ነው።

በዚህ ደብዳቤ ላይ ለምርጫው ምዝገባ መራዘም ቦርዱ አምስት ምክንያቶችን አስቀምጧል። እነዚህም የሕዝቡ የምርጫ ምዝገባ ግንዛቤ በበቂ ደረጃ ተደራሽ አለመሆን፣ የምርጫ ቁሳቁስ ለሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በእኩል ደረጃ ባለማዳረሱ፣ ወቅቱ የሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ወቅት በመሆኑ በአስመራጭ ቦርድ አባልነት የተመረጡ አባላቶች በዚሁ ሥራ ላይ በመሆናቸው፣ ሕዝቡ የምርጫ ምዝገባ ሲስተም ሥርዓት የተለመደ አለመሆንና ገና በመነቃቃት ላይ በመሆኑ እንዲሁም ከሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ ሙስሊም ማኅብረተሰብ እየቀረበ ያለው የምዝገባ ጊዜ መራዘም ጥያቄዎች መበራከታቸውን ነው።

በዚህም የመጅሊስ የ2017 ምርጫ በሁለት ሣምንት መራዘሙን የገለጸው ቦርዱ፣ የምዝገባ ማጠናቀቂያ ቀን ሐምሌ 13/2017 እንደሚሆን በመጥቀስ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚገኘው ሙስሊም ማኅበረሰብ በቀሩት ቀናት እንዲመዘገብ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ የ2017 ምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ የመራጮችን ምዝገባ ማካሔድ የጀመረው ሰኔ 13/2017 ነበር። (ሚንበር ቲቪ)

የፎቶ መግለጫ፡ የመጅሊስ ምርጫ ምዝገባ
የፎቶ ምንጭ፡ FMEB

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular