Homeዜናና ወቅታዊዜናአቢሲንያ አሚን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና መምሕራን ሽልማት አበረከተ

አቢሲንያ አሚን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና መምሕራን ሽልማት አበረከተ

አቢሲንያ ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት፤ በአቢሲንያ አሚን በኩል የሚያዘጋጀው ‘አሚን ስኩል አዋርድ’ ዛሬ ሰኔ 28/2017 በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት አበርክቷል። ባንኩ ሽልማቱን ያበረከተው በኮርዶቫ እና ረዛን አካዳሚ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ነው፡፡

በኮርዶቫ አካዳሚ ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል፣ በረዛን አካዳሚ ደግሞ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች ሽልማቱ ተበርክቷል።

በሁለቱም ትምህርት ቤቶች ከሁሉም ክፍሎች ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ እያንዳንዳቸው 10 ሺሕ ብር በአቢሲንያ አሚን ተበርክቶላቸዋል።

በትምህርት ቤቶቹ ለተማሪዎች ከአራት ሺሕ አስከ ሰባት ሺሕ ብር ሽልማት ያበረከተው ባንኩ ከተማሪዎች በተጨማሪ ከሁለቱም ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ ስድስት መምህራን ሽልማት አበርክቷል፡፡ አቢሲንያ አሚን ለመምህራኑ ያበረከተው የገንዘብ መጠን አስር ሺሕ ብር ነው፡፡

በኮርዶቫ አካዳሚ የሽልማት ሥነ ሥርዐት ላይ የተገኙት በአቢሲንያ አሚን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ቢዝነስ ሠርቪስ ዳይሬክተር አቶ አበጋዝ ይማም፣ የትምህርትን ልሕቀት ለማሳደግና ብቁ ተረካቢ ዜጋ ለማፍራት
ያለመ መሆኑን በገለጹት መርሐ ግብር፣ በዚህ ዓመትም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ዘጠኝ ትምህርት ቤቶች ላይ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ ሽልማቱን ለአራተኛ ዓመት አስቀጥለናል ብለዋል።

በተመሣሣይ ረዛን አካዳሚ በተከናወነው የሽልማት ሥነ ሥርዐት ላይ የተገኙት የአቢሲንያ ባንክ አቢሲንያ አሚን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ፕሮዳክት ዲቪዥን ማናጀር አቶ ሙሐመድ አሰፋ፣ ባንኩ በአቢሲንያ አሚን በኩል በበርካታ የማኅበረሰብ ተኮር ሥራዎች ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝና በትምህርት ቤቶቹ የተከናወነው የሽልማት ፕሮግራም የዚሁ አካል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአሚን ስኩል አዋርድ ዓላማ የትምህርትን ልሕቀትን ከፍ ከማድረግ ባለፈ፣ ተማሪዎችንና መምህራንን ላስመዘገቡት ውጤት የሞራል ድጋፍ በመስጠት እና ለወደፊቱ በዕውቀት ብቁ የሆነ ተረካቢ ዜጋ በማፍራት ረገድ አሻራ ለማስቀመጥ እንደሆነ አብራርተዋል።

አቢሲንያ አሚን በአዲስ አበባ ከተማ ሌሎች ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በሌሎች የክልል ከተሞች በአጠቃላይ በዘጠኝ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎችና መምህራን የሚያበረክተውን የማበረታቻ ሽልማት እንደሚቀጥል አስታውቋል።

በሥነ ሥርዐቱ ላይ ሽልማት የተበረከተላቸው ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው፤ ባንኩ ያበረከተው ሽልማት ለቀጣይ መንገድ ስንቅ እንደሚሆናቸው ተናግረዋል፡፡ የተማሪ ወላጆችም እንዲሁ ሽልማቱ ተማሪዎችን ውጤታማነት ከማስጠበቁ ባሻገር ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

ለተማሪዎች ሽልማት ያበረከተው አቢሲንያ ባንክ፣ ባንኩ የሸሪዐ መርሆችን በጠበቀ መልኩ በተቀማጭ፣ በብድር እና ሌሎች የአገልግሎት አማራጮችን በማቅረብ የደንበኞችን ቁጥር ከ2 ሚሊዮን በላይ ማድረስ ችሏል፡፡

አቢሲንያ ባንክ ከ2011 ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎቹን ወደ ሥራ በማስገባት በአሁኑ ጊዜ ከ69 በላይ የሚሆኑ ቅርንጫፎች በመላው ኢትዮጵያ በመክፈት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular