Homeዜናና ወቅታዊዜናሂጅራ ባንክ በሒሳብ ዓመቱ ከ1 ነጥ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ገቢ...

ሂጅራ ባንክ በሒሳብ ዓመቱ ከ1 ነጥ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ገቢ ማስመዝገቡ አስታወቀ

ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሚሰጠው ሂጅራ ባንክ፤ በ2024/25 የሒሳብ ዓመት ከ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ገቢ በማስመዝገብ ማጠናቀቁን ያስታወቀው ዛሬ ጁመዓ ሰኔ 27/2017 በዋና መሥሪያ ቤት በተሰጠ መግለጫ ነው፡፡ የባንኩ ኃላፊዎች እንደተናገሩት፤ ባንኩ ባለፈው ዓመት ካስመዘገበው ጠቅላላ ገቢ 148 ነጥብ 85 ፐርሰንት ዕድገት ያሳየ ነው፡፡

በባንኩ ሪፖርት መሠረት፤ ከትርፍ አኳያም ባንኩ ያስመዘገበው ትርፍ ከ840 ሚሊየን ብር በላይ ነው፡፡ ይህ ውጤት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 740 ፐርሰንት ጭማሪ የተመዘገገበት ነው። በዚህም የባንኩ ጠቅላላ ሐብት በ2024/25 የሒሳብ ዓመት ከ15 ቢሊዮን ብር በማለፍ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 95 ነጥብ 37 ፐርሰንት ጭማሪ አሳይቷል። እንዲሁም የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ወደ 12 ቢሊዮን ብር በማሳደግ 91 ነጥብ 4 በመቶ ውጤት ተመዝግቧል።

በተጨማሪም ባንኩ 40 ሚሊዮን ዶላር በማግኘት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 304 ነጥብ 5 ፐርሰንት ጭማሪ አስመዝግቧል፡፡ በአሁኑ ሰዓት 35 አዳዲስ ቅርንጫፎችን ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ 135 ቅርንጫፎች ደርሷል፡፡

የደንበኞችን ብዛት በተመለከተ ጠቅላላ የደንበኞች ቁጥር ወደ 931 ሺሕ 148 አድጓል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት የደንበኞች ብዛት አንጻር 69 ነጥብ 4 በመቶ የደንበኞች ጭማሪን ያሳየ ነው፡፡ ከዲጂታል አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ የኦምኒ ፕላስ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች ከ350 ሺሕ በላይ ደርሰዋል፡፡

በሌላ በኩል ባለፉት 6 ወራት ብቻ የሐላል ፔይ ዋሌት ተጠቃሚዎች ከ811 ሺሕ በላይ የደረሱ ሲሆን፤ በዲጂታል በኩል የተንቀሳቀሰው ገንዘብ ከ20 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡

ባንኩ በሪፖርቱ ሥራ ፈጣሪዎችን እና ታታሪ ወጣቶችን ለማበረታታት በማሰብ በ“ሚንበር ቲቪ” የሚተላለፈው “ሲራራ አዋርድ” የተሰኘ የውድድር መድረክ ማዘጋጀቱን በማስታወስ፤ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አኳያ፣ ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ተቋማት እና ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱንም አስታውቋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular