Homeዜናና ወቅታዊዜናቢቢሲ እስራኤል በጋዛ በፍልስጤማውያን ላይ በምትፈጽመው ጥቃት “የተጠና አድሏዊ ዘገባ” ሲያሠራጭ መቆየቱን...

ቢቢሲ እስራኤል በጋዛ በፍልስጤማውያን ላይ በምትፈጽመው ጥቃት “የተጠና አድሏዊ ዘገባ” ሲያሠራጭ መቆየቱን አዲስ ጥናት አጋለጠ

መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ያደረገው ብሪቲሽ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ቢቢሲ)፤ የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ በፍልስጤማውያን ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት በተመለከተ ባሠራጫቸው ዘገባዎች  “የተጠና አድሏዊ አሠራር” መከተሉን አዲስ ጥናት አጋልጣል፡፡

ጥናቱን ይፋ ያደረገው ‘ዘ ሙስሊም ካውንስል ኦፍ ብሪቴንስ ሴንተር ፎር ሚዲያ ሞኒተሪንግ’፤ ይህን ማረጋገጥ የቻለው የሀገሪቱ ብሔራዊ ጣቢያ እስልምናን እና ሙስሊሞችን በተመለከተ የሚሠሯቸው የዜና ይዘቶች ባደረገው ምርመራ” መሆኑን ገልጿል፡፡ እንደ ተቋሙ መረጃ ከሆነ፤ በዚህም ጣቢያው ያሠራጫቸው 35 ሺሕ ይዘቶች ላይ ምርመራ ተደርጓል፡፡

እ.አ.አ ከጥቅምት 7/2023 እስከ ጥቅምት 6/2024 ባለው ጊዜ ውስጥ በተመረጡ 3 ሺሕ 873 መጣጥፎች እና 32 ሺሕ 92 የቴሌቪዥን ይዘቶችን በመተንተን በተገኘው ውጤት፤ ቢቢሲ ከእስራኤል ወገን ጉዳት ደርሶባቸዋል ለተባሉ ግለሰቦች ከፍልስጤማውያን ጋር በንጽጽር ሲቀመጥ በአራት እጥፍ ‘ስሜት ኮርኳሪ’ ቃላትን ተጠቅሟል፡፡ በተጨማሪም “ጅምላ ጭፍጨፋ” የሚለውን አገላለጽ ከፍልስጤማውያን ይልቅ ከእስራኤል ወገን ጉዳት ደርሶባቸዋል ለተባሉት በ18 እጥፍ ጥቅም ላይ አውሏል፡፡

ጣቢያው ከዚህ ባሻገር በዘገባዎች ላይ ታሪካዊ እንዲሁም የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን አውድ (Context) ከማስቀመጥ ራሱን አቅቧል፡፡ ሚድል ኢስት ዐይ እንደዘገበው፤ በዚህ አግባብ ሆን ተብለው ከተዘለሉት መካከል ለአንዳንድ ክስተቶች መነሻ ተብለው የሚጠቀሱ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የተደረጉ የዘር ፍጅትን የሚቀሰቅሱ ንግግሮች ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም የፍልስጤሙ ሐማስ እ.አ.አ ጥቅምት 7/2023 በእስራኤል ላይ የሰነዘረው ጥቃት በድረ ገጽ በተሠራጩ 40 በመቶ ዜናዎች ላይ ተደጋግሞ ሲጠቀስ፤ የእስራኤል ወታደሮች የዌስት ባንክ፣ ጋዛ እና ምሥራቅ ቁድስን ከዐስርት ዓመታት በወረራ መያዛቸውን እንዲዘለል ተደርጓል፡፡

ከዜና ውጪ ቢቢሲ የሐማስን ጥቃት ለማውገዝ በማቀድ 38 ቃለ ምልልስ ያሰራጨ ሲሆን፣ የእስራኤል ወታደሮች የፈጸሙትን ጥቃት ለማውገዝ ይህን ከማድረግ ተቆጥቧል፡፡ የቢቢሲ ዜና አቅራቢዎች ጋዛ ከተማን ለመግለጽ የሚጠቀሙት “በሐማስ ቁጥጥር ስር ያለችው” በሚል እንደሆነ ያስታወሰው ጥናቱ፤ የእስራኤል ወታደሮች ከግማሽ በላይ የሚሆነውን አካባቢ በወረራ ቢይዙትም ድርጊቱ እንዳልተፈጠረ በማድረግ ሽፋን ሳይሰጡት አልፈውታል፡፡ በቃለ ምልልሶች ላይ ከእስራኤል ወገን የቀረቡት 2 ሺሕ 350 ግለሰቦች ሲሆኑ፤ ከፍልስጤም በኩል ቁጥሩ ከግማሽ በመቀነስ 1 ሺሕ 85 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ለጥናት ውጤት ምላሽ ሰጡት የቢቢሲ ቃል አቀባይ፤ በጋዛ ዘገባዎች ላይ ጣቢያው “ገለልተኛ ዘገባ” ሲያሠራጭ መቆየቱን በመጥቀስ የተከላከሉ ቢሆንም፤ የተደረገውን ምርመራ በአዎንታዊ ተቀብለን ሁሉንም ግብረ መልሶች እንገመግማለን ብለዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular