Homeዜናና ወቅታዊዜናበዐሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ የፍልስጤም ደጋፊዎች በጋዛ የሚፈጸመውን ጥቃት በመቃወም በሔግ ከተማ የተቃውሞ...

በዐሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ የፍልስጤም ደጋፊዎች በጋዛ የሚፈጸመውን ጥቃት በመቃወም በሔግ ከተማ የተቃውሞ ትዕይንተ ሕዝብ አካሔዱ

በኔዘርላንድስ ሔግ ከተማ የተገኙ በዐሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ የፍልስጤም ደጋፊዎች፤ በጋዛ የሚፈጸመውን ጥቃት የሚቃወም ትዕይንተ ሕዝብ ያካሔዱት ትናንት እሑድ ነው፡፡

ሠልፈኞቹ ዓለም አቀፍ ፍትሕ ፍርድ ቤት መቀመጫ በሆነችው ሔግ ከተማ ለተቃውሞ አደባባይ ሲወጡ፤ በአራት ሣምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ሠልፈኞቹ የሀገራቸው መንግሥት “ቀይ መስመር ታልፎ በጋዛ ጥቃት እየተፈጸመ በዝምታ አልፏል” ሲል ነቀፌታ መሰንዘራቸውን የሚድል ኢስት ዐይ ዘገባ አመልክቷል፡፡

በርካታ ሠልፈኞች የፍልስጤምን ሰንደቅ አላማ ሲያውለበልቡ በታዩበት ትዕይንተ ሕዝብ ላይ፤ “በእስራኤል የሚፈጸመው የዘር ፍጅት ይቁም” የሚል መፈክር በሥፋት ሲስተጋባ መስተዋሉን ተገልጿል፡፡ “ሌሎችን አትጠብቁ፣ ለተግባር ተንቀሳቀሱ”፣ “[ለእስራኤል] የዘር ፍጅት የኔዘርላንድ ተባባሪነትን ይቁም” እና “ዝም ማለት የሚኖርባችሁ ሕፃናት ሲገደሉ ሳይሆን ሲያንቀላፉ ነው” የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪ አምነስቲ አንተርናሽልን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶች ባስተባበሩት ትዕይንተ ሕዝብ ላይ፤ 150 ሺሕ ሰዎች መሳተፋቸውን አንደኛው አስተባባሪ ኦክስፋም አስታውቋል፡፡ የጋዛን እልቂት የሚቃወሙ ሠልፎች በተመሣሣይ በቤልጂየም፣ ቱርክ፣ ብራዚል እና ግሪክ መካሔዳቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ የሁሉም ተሳታፊዎች ጥያቄ በጋዛ የንጹሐን ሰቆቃ እንዲቆም መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

ፍልስጤምን የሚደግፉ ሰልፈኞች በአደባባይ በእስራኤል ላይ ተቃውሞ ባሰሙበት በዚህ ወቅት በጋዛ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 55 ሺሕ 362 መድረሱን የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት ቢያንስ 65 ንጹሐን መገደላቸውም በዘገባዎች ተጠቅሷል፡፡

ባለፉት ሦስት ሣምንታት ገደማ ብቻ የምግብ እደላ በሚካሄድባቸው ጣቢያዎች ተሰልፈው የነበሩ 2 ሺሕ 649 ንጹሐን በእስራኤል ወታደሮች ተገድለዋል፡፡ እነዚህ ማዕከሎች በራፋ እና ዋዲ ጋዛ የሚገኙ ናቸው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular