Homeዜናና ወቅታዊዜናወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎት መጀመሩን ይፋ አደረገ

ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎት መጀመሩን ይፋ አደረገ

ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ. በኢትዮጵያ በዘርፉ የመጀመሪያው አገልግሎት ሰጪ በመሆን ሥራ መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ የተገለጸው ማክሰኞ ግንቦት 26/2017 ምሽት በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በተዘጋጀው ሥነ ሥርዐት ላይ ነው።

በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዐቱ ላይ የኢንቨስትመንት ባንኩን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጨምሮ የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ጥላሁን እስማኢል፣ ምክትል ዳይሬክተሯ ሐና ተህልቁ፣ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር ዲኤታ ያስሚን ወሀበረቢ እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የተናገሩት የኢንቨስትመንት ባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አክሊሉ ውበት፣ ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ የካፒታል ገበያ ለኢኮኖሚ ዕድገት መፋጠን ያለውን ጉልህ አስተዋጽኦ በተገነዘቡ ተቋማት እና ዜጎች መመሥረቱን ገልጸዋል፡፡ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ብር 385 ሚሊዮን መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የኢንቨስትመንት ባንኩ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን መጋቢት ወር የሥራ ፈቃድ መረከቡን ያስታወሱት ሰብሳቢው፤ በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ግንቦት 6/2017 የንግድ አባልነት ምዝገባ በማከናወን ካፒታል ገበያውን በቀዳሚነት ተቀላቅሏል ብለዋል፡፡

በተመሣሣይ በመድረኩ ላይ የተናገሩት የወጋገን ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብሩታዊት ዳዊት፤ ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ በዘርፉ ፈር ቀዳጅ አሠራሮችን እያስቀመጠ “በታማኝነት እና በፈጠራ ላይ ተመርኩዞ” በሴክተሩ “ትርጉም ያለው ለውጥ እና ስኬት ለማስመዝገብ ይተጋል” ሲሉ የሚመሩትን ኩባንያ የወደፊት ዕቅድ አብራርተዋል፡፡

ወጋገን ባንክ ሥራ ያስጀመረው ወጋገን ካፒታል አክሲዮን ማኅበር ኢንቨስትመንት ባንክ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ሲቢኢ ካፒታል አክሲዮን የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ያገኙት መጋቢት 12/2017 እንደነበር ይታወሳል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular