Homeዜናና ወቅታዊዜናከግማሽ ሚሊዮን በላይ የፍልስጤም ደጋፊዎች፤ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ከእስራኤል ጋር ያለውን ግንኙነት...

ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የፍልስጤም ደጋፊዎች፤ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ከእስራኤል ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲያቋርጥ በሠልፍ ጠየቁ

ከመላው ዩናይትድ ኪንግደም የተሰባሰቡ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የፍልስጤም ደጋፊዎች፤ የሀገሪቱ መንግሥት ከእስራኤል ጋር ያለውን ግኙኑነት እንዲያቋርጥ በለንደን ጎዳናዎች ባደረጉት ሠልፍ ጠይቀዋል፡፡

ቅዳሜ እለት የተደረገው ሠልፍ መነሻ፤ ባለፈው ሣምንት 77ኛ ዓመቱን የደፈነው “መቅሰፍት” ወይም ፍልስጤማውያን “ነክበህ”በሚል ሥያሜ የሚጠሩት ክስተት መታሰቢያ ነው፡፡ ይህ ዓመታዊ መርሐ ግብር መሬታቸው በእስራኤል በወረራ ተይዞ ጥቃት የሚፈራረቅባቸው ፍልስጤማውያን ታስቦ የሚውል ነው፡፡ እ.አ.አ ሜይ 15/1948 በጀመረው በዚህ “መቅሰፍት”፤ አይሁዳዊያን በፍልስጤማዊያን ላይ ጦርነት ከፍተው በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩት ቀያቸውን ጥለው እንዲሸሹ ማደረጋቸውን የታሪክ ድርሳናት ያመለክታሉ፡፡

ዌልስ እና ሰሜን ኢንግላንድን ጨምሮ ከሁሉም የዩናይትድ ኪንግደም አካባቢዎች የተገኙ የፍልስጤም ደጋፊዎች በተሳተፉበት ሠልፍ ላይ፤ በአሁኑ ሰዓት በጋዛ የቀጠለው ጥቃት እንዲቆም ጥሪ ቀርቧል፡፡ 600 ሺሕ ገደማ የተገመተው የሠልፈኞች ቁጥር ከባለፈው ዓመት ጥቅምት ወዲህ በቁጥር ከፍተኛው መሆኑን ሚድል ኢስት ዐይ ዘግቧል፡፡

የሠልፉ አስተባባሪዎች የፓለስታይን ሶሊዳሪቲ ካምፔይን፣ ፍሬንድስ ኦፍ አልአቅሷ፣ ዘ ሙስሊም አሶስዬሽን ኦፍ ብሪቴን፣ ዘ ፓለስቲንያን ፎረም ኢን ብሪቴን እና ሌሎች የፍልስጤም መብት ተሟጋች ድርጅቶች ናቸው፡፡ አንደኛው አስተባባሪ ፓለስታይን ሶሊዳሪቲ ካምፔይን፤ ሠልፉ የተደረገው ዩናይትድ ኪንግደም በጋዛ የሚፈጸመውን የዘር ፍጅት እንድታስቆም ጥሪ ለማቅረብ በሚል ዓላማ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ባለፈው ሣምንት ታስቦ በዋለው “መቅሰፍት” መነሻ ፍልስጤማውያን ላለፉት 77 ዓመታት በመሬታቸው ላይ ለመንቀሳቀስ ጭምር ፍቃድ እንዲጠይቁ ተገደዋል፡፡ በወቅቱ ጥቃት መከፈቱን ተከትሎ አዲስ የተቋቋመው የእስራኤል መንግሥት 78 በመቶውን በታሪክ የፍልስጤም ተብሎ የተሰመረውን የፍልስጤም ግዛት መውረሱን ዘገባው አመልክቷል፡፡ እስራኤል በተለይ ከ1995 ወዲህ በወረራ የያዘችውን ዌስት ባንክን በሦስት ክፍል በመሸንሸን በ700 ሺሕ ሠፋሪዎች በመሙላት ፍልስጤማውያን በአንድ አካባቢ እንዲወሰኑ አድርጋለች፡፡ በዌስት ባንክ እስራኤል የራሷን ሰዎች በሕገ ወጥ መንገድ ስታሠፍር ከዐስር ሺሕ በላይ የፍልስጤማውያን ግንባታዎችን በማውደም ነው፡፡

መሬታቸው ባዕድ የተወረረባቸው ፍልስጤማውያን፣ ወደ ሥራ ሊሄዱ ሲሉ የይለፍ ፍቃድ ለማግኘት በማለዳ መሰለፋቸውም የዕለት ውሏቸው አካል ሆኖ እነዚህ ሁሉ ዓመታት ማለፉንም ዘገባው አስታውሷል፡፡ እስራኤል የፍልስጤማውያኑ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ጥላ ሥማቸው በሥራ ማጣት ከዓለም ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular