Homeዜናና ወቅታዊዜናከፓኪስታን የሚነሱ ሑጃጅ የአውሮፕላን በረራ ተራዘመ

ከፓኪስታን የሚነሱ ሑጃጅ የአውሮፕላን በረራ ተራዘመ

ሕንድ እና ፓኪስታን በገቡበት ውጥረት ሳቢያ በዛሬው እለት ሊደረግ የነበረው ከፓኪስታን የሚነሱ ሑጃጅ የአውሮፕላን በረራ መራዘሙን የሀገሪቱ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡ የሑጃጅ በረራ የተሰረዘው አየር መንገዱ ለቀጣይ 12 ሰዓታት የበረራ እግድ በመጣሉ ምክንያት መሆኑን ዐረብ ኒውስ ዘግቧል፡፡

በሀገራቱ መካከል በተከሰተው ከፍተኛ ውጥረት ሳቢያ በፓኪስታን ዋና ዋና አየር ማረፊያዎች ናቸው የሚባሉት ካራቺ፣ ላሆር እና ኢስላማባድ ለጊዜው አገልግሎት እንዳይሰጡ መደረጋቸውም ተሰምቷል፡፡ በረራዎቹ የተሰረዙት ሕንድ በፓኪስታን ሦስት ግዛቶች ላይ ከፈጸመችው የሚሳኤል ጥቃት በኋላ ነው፡፡ በንጹሐን ላይ ከተፈጸመው ግድያ በተጨማሪ በሦስት መስጂዶች ላይ ውድመት ማድረሱ የተነገረው ጥቃት የተሰነዘረው ባሃዋልፑር፣ ኮትሊ እና ሙዛፋራባድ በተባሉ ግዛቶች ነው፡፡

ከዚሁ ውጥረት ጋር በተገናኘ የጃሙ እና ካሽሚር ግዛት ሐጅ ኮሚቴ፤ ዛሬ ረቡዕ እና በነገው እለት ሊደረጉ የነበሩ የሑጃጅ በረራዎችን መሠረዙን ይፋ አድርጓል፡፡ የሐጅ ኮሚቴው ዋና ኃላፊ ዶክተር ሹጅሃት አሕመድ እንደተናገሩት፤ በረራዎቹ የተሠረዙት የሲሪናጋር አየር ማረፊያ በመዘጋቱ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular