ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት፤ ለ22 ዓመታት ለደንበኞቹ የድምጽ እና ቪዮ ጥሪ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ስካይፕ (Skype) ዛሬ ሰኞ እንደሚዘጋ አስታውቋል፡፡
እ.አ.አ በ2003 ሥራ አገልግሎት መስጠት የጀመረው መተግበሪያው፤ ደንበኞች የድምጽ እና ቪድዮ መልዕክት ለመለዋወጥ በፈር ቀዳጅነት እንዲሁም በጥራት የሚመርጡት ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ባለፉት ዓመታት ከቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር የተስፋፉትን እንደ ዙም (ZOOM) እና ዋትሳፕ (Whatsapp) ያሉ ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡ መተግበሪያዎችን መፎካከር አለመቻሉን ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ የስካይፕ እናት ኩባንያ እንዳለው ከሆነ፤ “የመተግበሪያው ዕድሜ ማብቂያው ላይ ደርሷል”፡፡ በዚህ ምክንያት ከዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 27/2017 (ሜይ 5/2025) አንስቶ ሥራ ያቆማል፡፡
መተግበሪያ ከፍተኛ ተጠቃሚዎችን ባስመዘገበበት ከዐስር ዓመት በፊት በአንድ ወር 300 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ነበሩት፡፡ (ሚንበር ቲቪ)












