Homeዜናና ወቅታዊዜናየመጀመሪያዎቹን ሑጃጅ በነገው ዕለት እንደምትቀበል ሳዑዲ ዐረቢያ አስታወቀች

የመጀመሪያዎቹን ሑጃጅ በነገው ዕለት እንደምትቀበል ሳዑዲ ዐረቢያ አስታወቀች

በዘንድሮ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ላይ የሚሳተፉ ቀዳሚዎቹ ምዕመናን በነገው እለት ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ እንደሚጓዙ ታውቋል። ለክንውኑ በቀዳሚነት ወደ ሀገሪቱ የሚገቡት የደቡብ አፍሪካ ዜጎች እንደሚሆኑ ይፋ ተደርጓል።

ደቡብ አፍሪካውያኑ ነገ ሰኞ ሚያዝያ 20/2017 ከመግባታቸው አስቀድሞ ምዕመናኑን ለመቀበል ጁመዓ ዕለት አስተባባሪዎችን ያካተተ ልዑክ ወደ ጂዳ ከተማ መጓዙን የሀገሪቱ ሐጅ እና ዑምራ ምክር ቤት በኤክስ ገጹ ያጋራው መረጃ ያመለክታል። ከደቡብ አፍሪካ በክንውኑ ላይ የሚሳተፉ ምዕመናን ቁጥር 2 ሺሕ 500 መሆኑ ተገልጿል። ምዕመናኑ ጂዳ ከተማ በማረፍ ወደ ቅዱሳኑ መዲና እና መካ ይጓዛሉ ተብሏል።

በማግሥቱ ማክሰኞ ከደቡብ አፍሪካውያን በመቀጠል የሦስት ሀገሮች ዜጎች ይከተላሉ ተብሎ ይጠበቃል። እነዚህ ምዕመናን ከፓኪስታን፣ ሕንድ እና ባንግላዴሽ የሚነሱ ይሆናሉ።

ረቡዕ ደግሞ በሐጅ ሥነ ሥርዐት ላይ በቁጥር በርካታ ምዕመናንን የምታሳትፈው ኢንዶኔዥያ ዜጎቿን ትልካለች ተብሎ እንደሚጠበቅ የሳዑዲ ዐረቢያ ባለሥልጣናት ገልፀዋል። ከኤንዶኔዥያ በዘንድሮ ዓመት ለሐጅ የተመዘገቡ ምዕመናን ቁጥር 221 ሺሕ ነው።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ በዘንድሮ የሐጅ ሥነ ሥነ ሥርዐት ክንውን ላይ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን በረራ የሚጀመርበትን ቀን ባለፈው ሰኞ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በምክር ቤቱ የሐጅ እና ዑምራ ዘርፍ ይፋ በተደረገው መሠረት የምዕመናን በረራ ግንቦት 6 ተጀምሮ፣ ግንቦት 30/2017 ይጠናቀቃል።

በሐጅ ሥነ ሥርዐት ላይ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ምዕመናንን ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቀደም ብለው የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular