Homeዜናና ወቅታዊዜናማልዴቪዝ በጋዛ ንጹሐን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በመቃወም የእስራኤል ፓስፖርት የያዙ ግለሰቦች ወደ...

ማልዴቪዝ በጋዛ ንጹሐን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በመቃወም የእስራኤል ፓስፖርት የያዙ ግለሰቦች ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ ዕግድ ጣለች

እስልምና ብሔራዊ ሃይማኖት በሆነባት ማልዴቪዝ፤ የእስራኤል ፓስፖርት የያዙ ግለሰቦች እንዳይገቡ ዕግድ ተጥሏል፡፡ የደሴቱቱ ፓርላማ ዕግዱን የጣለበትን ሕግ ያጸደቀው፤ በጋዛ በንጹሐን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በመቃወም ነው፡፡

የማልዴቪስ ፓርላማ ዕግዱን ካጸደቀ በኋላ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሙሐመድ ሙኡዚ ባለፈው ሰኞ ፊርማቸውን እንዳኖሩበት ሚድል ኢስት ዐይ ዘግቧል፡፡ የሙኡዚ ካቢኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ደሴቲቱ እንዳይገቡ ውሳኔ ያሳለፈው ከዐሥር ወራት በፊት የነበረ ቢሆንም ውሳኔውን ተግባራዊ ሳይደረግ ቆይቷል፡፡

ከዚህ አስቀድሞ ዋንኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ማልዲቭያን ዴሞክራቲክ ፓርቲ አባሉ ሚካኢል አሕመድ ናሲም፤ ክልከላውን የሚጥለው የሀገሪቱ የኢሚግሬሽን ሕግ እንዲሻሻል የውሳኔ ሐሳብ አቅርበው ነበር፡፡ በወቅቱ የቀረበው ሐሳብ ከ300 ቀናት በኋላ ጸድቆ ከማግሥቱ ጀምሮ ተፈጻሚ እንዲሆን ተደርጓል፡፡  

ከውሳኔው በኋላ የፕሬዝዳንት ሙሐመድ ሙኡዚ ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፤ “የፀደቀው ሕግ መንግሥት ለጭካኔ ድርጊቶች እና እስራኤል በፍልስጤም ሕዝብ ላይ ለፈጸመችው የዘር ማጥፋት ድርጊት ምላሽ ለመስጠት የተወሰደውን ጠንካራ አቋም የሚያንፀባርቅ ነው” ብሏል፡፡

በዘገባው መሠረት ማልዲቭስ የእስራኤል ፓስፖርት የያዙ ግለሰቦችን ላይ የጉዞ እገዳ ስትጥል ይህ የመጀመሪያው አይደለም። 1 ሺሕ 129 ደሴቶችን የያዘችው ማልዴቪስ፤ እ.አ.አ በ1965 ከእስራኤል የሀገርነት እውቅና ማግኘቷል ተከትሎ በምላሹ በተመሣሣይ ለእስራኤል የሀገርነት ዕውቅና ብትሰጥም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ የቆየው ለስምንት ዓመታት ብቻ እስከ 1974 ነበር፡፡ ተጥሎ የቆየው ዕግድ በ1990ዎቹ በተፈረመ ዳግም ስምምነት እንዲነሳ ተደርጎ እስከ 2018 ድረስ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ከዚያ በኋላ የሁለቱ ግንኙነት መልካም ተብሎ የሚገለጽ አለመሆኑ ይነገራል፡፡

ማልዴቪስ በ2024 ከመላው ዓለም ሁለት ሚሊዮን ገደማ ቱሪስቶችን አስተናግዳለች፡፡ ደሴቲቱን ከጎበኙት ሀገሮች ዜጎች መካከል ቀዳሚውን ሥፍራ የሚይዙት ቻና፣ ጣሊያን፣ ሕንድ፣ ሩስያ እና ዩናይትድ ኪንግደም ናቸው፡፡ በአሕጉር በርካታ ቱሪስቶች የተጓዙት ከአውሮፓ ነው፡፡

በበርካታ የባህር ዳርቻዎች እና ውብ ሐይቆች የምትታወቀው ማልዴቪስ፤ በዓለም ላይ ካሉ ዋና ዋና የቱሪስት መዳረሻዎች ተጠቃሽ ነች፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular