Homeዜናና ወቅታዊዜናሳዑዲ ዐረቢያ ከሚያዝያ ወር መገባደጃ ጀምሮ ዑምራ መፈጸም የሚችሉት የሐጅ ቪዛ የያዙ...

ሳዑዲ ዐረቢያ ከሚያዝያ ወር መገባደጃ ጀምሮ ዑምራ መፈጸም የሚችሉት የሐጅ ቪዛ የያዙ ምዕመናን ብቻ እንደሚሆኑ አሳወቀች

የሳዑዲ ዐረቢያ ሐጅ እና ሚኒስቴር፤ ከሚያዝያ 21/2017 (ዙል ቀዕዳህ 1/1446 ዓ.ሂ) ጀምሮ እስከ ግንቦት 27/2017 (ዙል ሒጃ 14/1446 ዓ.ሂ) ድረስ በሚኖሩ 42 ቀናት፤ በዑምራ ሥነ ሥርዐት ክንውን ላይ መሳተፍ የሚችሉት የሐጅ ቪዛ ያላቸው ምዕመናን ብቻ እንደሚሆኑ አሳውቋል፡፡

እንደ ሚኒስቴሩ ከሆነ፤ ይህ ተፈጻሚ የሚደረገው በሀገሪቱ ዜጎች፣ በነዋሪነት የተመዘገቡ የውጪ ሀገሮች ዜጎች እንዲሁም ከሐጅ ውጪ ማንኛውም የቪዛ ዐይነት በእጃቸው ላይ በሚገኙ ምዕመናን ላይ ነው፡፡

ውሳኔው የተላለፈው በሐጅ ወቅት የሚኖረውን መጨናነቅ ለመቀነስ እንዲሁም በዑምራ እና በሐጅ ክንውን መካከል መደራረብ እንዳይኖር እና ዓመታዊውን የሐጅ ክንውን በተሻለ መልኩ ለማስተናገድ በሚል ነው፡፡ ለተፈጻሚነቱ ያግዛል በሚል በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ የዑምራ ቪዛ ሙሉ ለሙሉ መስጠት የሚቆም ይሆናል፡፡

የጉዞ ወኪሎች እና አገልግሎት ሰጭዎች ለምዕመናን የተደረጉ የአሠራር ለውጦችን ቀድመው እንዲያሳውቁ ሚኒስቴሩ ማሳሰቡን የኢስላሚክ ኢንፎርሜሽን ዘገባ ያመለክታል፡፡

ሳዑዲ ዐረቢያ በተመሣሣይ በሐጅ ወቅት የሚኖረውን መጨናነቅ ለመቀነስ በሚል በ14 ሀገሮች ላይ የዑምራ፣ የቤተሰጥ ጥየቃ እና የንግድ ቪዛ ዕግድ መጣሏ ይታወሳል። ባለፈው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ላይ ከመላው ዓለም ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ምዕመናን ተሳታፊ ሆነዋል። (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular