Homeዜናና ወቅታዊዜናየዑምራ ተጓዥ ምዕመናን በሀገሯ መቆየት የሚችሉት ለቀጣይ ሦስት ሣምንታት ብቻ እንደሚሆን ሳዑዲ...

የዑምራ ተጓዥ ምዕመናን በሀገሯ መቆየት የሚችሉት ለቀጣይ ሦስት ሣምንታት ብቻ እንደሚሆን ሳዑዲ ዐረቢያ አስታወቀች

የሳዑዲ ዐረቢያ ሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር፤ ለዑምራ የገቡ ምዕመናን በሀገሪቱ መቆየት የሚችሉት ለቀጣይ ሦስት ሣምንታት ብቻ እንደሚሆን አስታወቀ፡ ሚኒስቴሩ ይህን ይፋ ያደረገው ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 30/2017 ባወጣው መግለጫ ነው፡፡

መግለጫው ምዕመናን ለዑምራ ክንውን ወደ ሀገሪቱ መግባት የሚችሉት እስከ መጪው እሑድ ሚያዝያ 5/2017 (ኤፕሪል 13/2025) ድረስ ብቻ እንደሚሆን ያመለክታል፡፡ እነዚህ ምዕመናን በሳዑዲ መሬት መቆየት የሚችሉት እስከ ሚያዝያ 21/2017 (ኤፕሪል 29/2025) ድረስ ብቻ እንደሚሆንም ተጠቅሷል።

የዑምራ ጉዞ የሚያሳልጡ ኩባንያዎች፣ ግለሰቦች እና አገልግሎት ሰጪዎች የተቀመጠውን የጊዜ ሠሌዳ በጥብቅ እንዲከተሉ ያሳሰበው የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር፤ ከተጠቀሰው ጊዜ በላይ በሳዑዲ ግዛት ውስጥ መቆየት “እንደ ሕግ ጥሰት የሚቆጠር በመሆኑ” ኩባንያዎች 100 ሺሕ የሳዑዲ ዐረቢያ ሪያል ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚችል አስፍሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሕግ ተጠያቂነት ይከተላል ሲል አስጠንቅቋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
ታላቅ ግብዣ

Most Popular